Logo

የኢዴፓ የሥራ አስፈፃሚ የክልል ቢሮዎች ጉብኝት

February 15, 2014

የኢዴፓ የሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ወንድወሰን ተሾመና አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ከታህሳስ 25 ቀን  2006 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ለስድስት ቀናት የቆየ የሥራ ጉብኝት በደሴና በላሊበላ አካሄዱ፡፡ በዚህም ጉብኝት በመጀመሪያ በደሴ አራዳ ገበያ አካባቢ ያለውን ቢሮ የተመለከቱና ቢሮውንም እንዳዲስ ያጠናከረ ሲሆኑ በመቀጠልም በላሊበላ ከተማ ቀደምት በሚባለው ቦታ አካባቢ የሚገኘውን ቢሮ ከተመለከቱና በዛው የሚገኙ አባላትና የኮሚቴ አመራሮችን በፅህፈት ቤትና ከፅህፈት ውጪ በማግኘት ያነጋገሩና የሥራ መመሪያ ያስተላለፉ መሆኑ ታውቋል፡፡

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሴያዊ ፓርቲ (ኢ.ዴ.ፓ) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ እና የፋይናንስ ኃላፊ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ ባልከው እና አቶ አዳነ ታደሰ በሐረር እና በድሬደዋ ከተሞች የፓርቲውን ጽ/ቤት መዋቅር እና የማጠናከር ሥራ ከጥር 27 ቀን 2006 ዓ. ም እስከ ጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም  ሰርተው ተመልሰዋል፡፡

አመራሩ በሐረር ጽ/ቤት ጉዳይና አካባቢው ላይ ያለውን እንቅስቀሴ በምን መልክ ማጠንከር እንደሚችል ከሐረር ኮሚቴ ጋር ገንቢ ውይይት ያደረገ ሲሆን አመራሩ ኮሚቴውን ከላይ ሆኖ ተከታታይ ድጋፍና ክትትል ቢያደርግለት ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ለአመራሩ አረጋግጠዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ከሐረር ጉዞ በኋላ ማለትም በጥር 29 ቀን 2006 ዓ.ም አመራሩ ወደ ድሬደዋ ገብቶ ከድሬደዋ ኮሚቴ ጋር ውይይት ያድረገ ሲሆን፡ የድሬደዋ ኮሚቴ ከሐረር ቢሮ ጋር በመገናኘት በአንድ ላይ ስለሚሰሩበት መንገድ እና በድሬደዋ ከተማ ያለውን እንቅስቃሴ በቀጣይ የሚጠናከርበትን ሁኔታ ላይ ውጤታማ ውይይት አድርጎ በጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ አዲስ አበባ  ተመልሷል፡፡

Source- Ethiopian Democratic Party

Share