ይድረስ ለፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
ሟቾችም እኛው፣ ገዳዮችም እኛው፣ መስካሪዎች እኛው፣ ፈራጆችም እኛው – ማን ይቅርታ ይጠይቅ?
(ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የፓርላማ አባል)
Email: ahayder2000@gmail.com
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ የተባሉ “ምሁር” ባለፈው ሰሞን “እርቅና ሰላም፤ የህይወት ቅመም” በሚል ርዕስ በተለያዩ ድረ-ገፆች ያሰራጩት መዘዘኛ ጽሑፍ ነው፡፡ የፕሮፌሰሩ የጽሑፍ ርእስ አሳሳች ነው፡፡ “እርቅና ሰላም፤ የህይወት ቅመም” የሚለውን ርእስ ከስሩ ካለው የደስ ደስ ያለው የአዛውንት ፎቶግራፍ ጋር የሚያይ ሰው፤ በሕዝቦች መካከል ጦርነት የሚቀሰቅስ መልእክት ይኖረዋል ብሎ ሊጠረጥር አይችልም፡፡