Logo

የአማርኛ ምሣሌያዊ አነጋገሮች

1 ሳይከካ ተቦካ
2 ቀና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ
3 አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል
4 አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል
5 ያለ አንድ የላት ጥርስ በዘነዘና ትነቀስ
6 የምታቦካው የላት የምትጋግረው አማራት
7 የጅብ ፍቅር እስኪቸግር
8 አላርፍ ያለች ጣት ስትጠነቁል ትያዛለች
9 በሬ ከአራጁ ይውላል
10 በቅሎ ግዙ ግዙ አንድ አሞሌ ጨው ላያግዙ
11 ዘመድ ከዘመዱ አህያ ከአመዱ
12 ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
13 አይጥ ሞቷን ስትሻ ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ
14 ከድጡ ወደ ማጡ
15 የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል
16 የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ
17 አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል
18 በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት
19 አልሸሹም ዞር አሉ
20 ታጥቦ ጭቃ
21 የቆጡን አወርዳለሁ ብላ የብብቷን ጣለች
22 ለሰው ብሎ ሲያማ ለኔ ብለህ ስማ
23 ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይከፋሽ
24 ባጎረስኩት እጄ ምነው መነከሴ
25 እጸድቅ ብዬ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች
26 ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል
27 ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ፀሎት
28 ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም
29 የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል
30 አያዘልቅ ፀሎት ለቅስፈት
31 ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ
32 ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ
33 ያልጠረጠረ ተመነጠረ
34 አዛኝ ቅቤ አንጓች
35 ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ
36 ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ
37 ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል
38 አህያውን ፈርቶ ዳውላውን
39 ሴት የላከው ሞት አይፈራም
40 ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል
41 ስራ ለሰሪው እሾህ ለአጣሪው
42 አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ
43 ተልባ ቢንጫጫ በአንድ ሙቀጫ
44 አመድ በዱቄት ይስቃል
45 ላለፈው ክረምት ቤት አይሰራለትም
46 የፈሰሰ ውሀ አይታፈስም
47 አትሩጥ አንጋጥ
48 መቀመጥ መቆመጥ
49 ካለ ፈጣሪ አሟጠሽ ጋግሪ
50 የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው
51 ስጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አንድ አለ
52 ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ
53 አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት መጽሀፍ አጥባ ቆየች
54 የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ
55 እሱ የከፈተውን ጉሮሮ ሳይዘጋው አያድርም
56 ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ
57 አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ
58 ንገረው ንገረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው
59 አታግባና የሰው አጥር ዝለል
60 ከስስታም አንድ ይወድቀው አንድ ይተርፈው
61 ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት
62 ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል
63 አተርፍ ባይ አጉዳይ
64 አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል
65 የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ
66 ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል
67 ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሀምሳ ሰው ጌጡ
68 እውነቱን ተናግሮ ካመሹበት ማደር
69 ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
70 ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል
71 ከእጅ አይሻል ዶማ
72 በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ
73 የአህያ ባል ከጅብ አያስጥል
Share