በህግ አምላክ ክፍል 2፤ ኦርቶዶክስና እስልምና ምን አደረጉልን?
ያሬድ ኃይለመስቀል
ባለፈው ስለ ኢትዮጵያ ቤተ እምነቶች ለነጻነታችን ምን ያህል አስተዋጻኦ እንደነበራቸው። የግዕዝ ፊደልና በቤተ እምነት ዙሪያ የተፈጠሩት ትምህርት ቤቶች ምን ያህል ለሀገራችን ህዝብ አብርሆት እና ለዓለማቀፍ እውቀት ቋት እንዳበረከቱ ተገልጻል። በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ የሚያውቁ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርሥቲያን ጳጳሳት ሊቃውንት እና የእስልምና ምሁራን አሉ። ይሁንና ፈርተውም ይሁን ወይም የጥቅም ግጭት ተፈጥሮባቸው “ለመሆኑ ለ2ሺ ዘመን ምን አስተዋጽኦ አደርጋችሁ?” ተብለው ሲዘለፉ ብዕራቸውን ያነሱ እስካሁን አልታዩም። እነሱ ንቀቱ ባይሰማቸውም እኛ ደቂቶቹ መዕመናኖቹ የአቅማችንን እንሞክር።
እኔ የምጽፈው፡
1ኛ፡ እራሴ አንድ ነከር ሲኮረኩረኝ መረጃ እንድፈልግ እንዳነብና ለመረዳት ስለሚያግዘኝ ነው። 2ኛ፡ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር “ምሁራኑ” የተሳሳተውን ትርክት ለማረም ባለመሞከራቸው ውሸቱ እውነት አየሆነ ትውልድ እየጠፋ ነው። ያሁኑ የራስ ጥላቻ ትርክት 50 ዓመታት ፈጅቶ ነው እዚህ የደረሰው፣ ይሄንን ለመቀልበስ ደግሞ ሌላ 20 ዓመታት ይፍጅ ይሆናል። ስለዚህ ዛሬ ሁሉም መረባረብ አለበት። የራስ ጥላቻ ትርክት አጥፍተን በኢትዮጵያዊነቱ፤ በጥቁርነቱ፤ በአፍሪካዊነቱ እንዲኮራ አድርጎ ማስተማር የቤተሰብ ግዴታ ነው። ቤተሰብ ደግሞ መረጃ ይፈልጋል። ለኔ ስነልቦና አያቶቼ እና ቤተሰቦቼ እንጂ የደርግ ግዜ ትምህርት ቤት አይደለም የቀረጸኝ። ስለዚህ የምናውቀውን ማጋራት፤ ለልጆቻችን ማስተማር እንደአሁኖቹ ፓለቲኪኞች አዲስ እራሱን የማይጠላ እና የማይንቅ ትውልድ መፍጠር ያስፈልጋል። ጽሁፏን ከወደዳችሁት ለወጣቶች አጋሯት።
ዘለፋውና ማና’ናቁ
“እብድና ዘመናይ የልቡን ይናገራል” ይባላል። እብድ ማመዛዘን ስለማይችል ዘበናይ ደግሞ ሁሉንም ስለሚንቅ ለማለት ነው። ሌላው ፕሮፌሰር መስፍን “ፈረንጅ እውቀት ሀይል ነው” (knowledge is power) የሚለው አባባል እኛ ሀገር ሲደርስ ተገልብጦ “ስልጣን እውቀት ሆነ” (Power is Knowledge) ይሉ ነበር።
ጠመንጃና ጉልበት ያለው ሰው “አዋቂና አስተማሪ” ልሁን ይላል። ሁሉም የፈረንጅ መሪ ብዙ የንግግር ጸሀፊ አለው። ንግግሩ በባለ እውቀቶች ተጽፎ ታርሞ ነው። ለምሳሌ “አክሱም ለወላይታ ምኑ ነው? “ወርቅና ጨርቅ” አቶ መልስ በማለታቸው እስከዛሬ ይተቹበታል?
ህዝብ ደግሞ የመሪን ስህተት ካላሳየ ሰውዬው ትክክል ነኝ ብሎ ያስባለ። ስልጣን እውቀት መሆን ከጀመረ የዛሬ 50 ዓመት ነው። ሻለቃ መንግስቱ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ ናቸው ይባላል ይሁንና እነ ዶ/ር አሻግሬ ይግለጡን፤ እነ ዶ/ር አለሙ አበበን፤ እነ ኮ/ል ጎሹ ወልዴን ቁጭ አድርገው ያስተምሩ ነበር። አሁንም ይህ ባህል ቀጥሎ እነ ዶ/ር ጌዲዮን ቲሞቲዎስን፤ እነ ፕሮፌሰር አለማርያምን፤ እነ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋም በኮለኔል አብይ አህመድ በፕሮጀክተር ትምህርት ከተሰጥቷው ቦሀላ ፈተና ተፈተኑ ሲባል ሰምተናል። ፈተናው ወረቀት ታርሞ ውጤቱ ይገለጣል ብለን ስንጠብቅ ሚስጢር መደረጉ ማናልባት ፈተናውን ወድቀው ይሆናል ብለን እንድናስብ አድርጎናል።
ይሄንን ባለ ስልጣን የእውቀት ምንጭ ነው የሚለውን ባህል ለማስቆም ያስፈልጋል። ፓርላማ የማስተማሪያ አዳራሽ ሳይሆን የመከራከሪያ ነው። መማር የሚፈልግ ትምህርት ቤት እንጂ ፓርላማ መግባት የለባቸውም። ጳጳሳቱ፥ ዑስታዞቹ፥ የፓርላማ አባላቱ፥ የዩኒቨርሲቲ ምሁራኑ በባለሥልጣን የተነገረ ሁሉ የአግዚአብሔር ቃል ይሆናል ብለው ሐሰትን ሐሰት፥ እውነትን እውነት ካላሉ እንዴት ትውልድ እውነትና ከውሸት ይለያል?
ወደ ትችቱ ስመለስ ዛሬ የመረጥኩት ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ የሚለውን አባባል ይዤ ነው።
የፈረንጅ አምልኮ “ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ”
በአጭሩ፡ በዳርዊን ሳይንስ የእኛ ምድባቸን ከዝንጀሮ እንጂ ከሰው አልነበረም። እኛንም መላውን የአፍሪካ ህዝብ ከዝንጀሮነት ወደ ሰውነት ምደባ እንድንሸጋገር ያደረገችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለሺ አመታት ያከማቸችው የሀሳብ ክምችት ነው። እንዴት ማለት ደግ ነው?
“ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ” ማለት ሌሎች ስለ እኛ የሚሰጡትን አስተያየት ብንሰማ ኖሮ እናፍር ነበር ለማለት ነው። የኛም ፓለቲከኞች ስለነሱ ፈረንጆቹ የተጻፉትን ቢያነቡ ኖሮ በፈረንጅ አምልኮ ባልተለከፉ ነበር።
ፈረንጆቹ የጻፉት ጥቁሩ ህዝብ በዝግመተ ለውጥ ከዝንጀሮ ትንሽ ሻል ያለ ፍጥረት እንጂ ሰው አይደለም ብለው በርካታ የኢሮፕ ሳይንቲስቶች፤ አንትሮፓሎጂስቶች ወፋፍራም መጽሀፍ ጽፈው ዓለምን ሁሉ አሳምነው ነበር። በትንሹ ለመጥቀስ ቻርልስ ዳርዊን (Charles Darwin, “The Descent of Man” (1871)); ሀርበርት ስፔንሰር (Herbert Spencer “Survival of the Fittest” in Principles of Biology); ኤድዋርድ ቴይለር (Sir Edward Tylor, “Primitive Culture” (1871), the theory of cultural evolution), ማለትም በ(Civilized Nations) የሰለጠነ ብሄር፥ Barbarians (ብሄረሰቦች)፥ Savage (ህዝቦች) ተብሎ የተቀዳውና ስድብ እኛ በህገመንግስታቸን የተካተተው ነው።
አቶ መለስ ዜናዊ ይህንን ስድብ ምንጩ ምን እንደሆነ ሳያጣሩ ቀድተው አሁን በባህል ዝግመተ ለውጥ ደቡብ ህዝብ ከዐምሓራና ከኦሮሞና ትግሬ ላይ ያልደረሰ አረመኔ በሚለው ተመድቧል። ከአረመኔነት ወደ ብሄርነት በዝግመተ ለውጥ የሚሸጋገር እንደሆነ ካድሬው እንዲለማመደው አደረጉ። አሁንም በ ዶ/ር አብይ አህመድም ይሄንኑ አስቀጥለዋል። የተሰደቡት እነ አቶ ሬዲዋንም ሳይቀር ይህንን ህገመንግስት የነካ ባይኔ መጣ እያሉ ነው።
ፍራንሲስ ጋልተን ደግሞ ( Francis Galton (1822-1911) ስለ “Eugenics” 1883) አስፈላጊነት ጽፏል። ይህ ቃል በአማርኛ አላውቀውም። ይህ ማለት በዝግመተ ለውጥ ወደፊት የሄደው የነጩ ዘር በዝግመተ ለውጥ ወደ ኋላ ከቀረው ጋር ማለትም ከዝንጀሮ ጋር እንዳይዳቀልና ወደሃላ እንዳይመልስ የሚያስፈልገው ይሂንን የዝንጀሮ ዘረ መል ማጥፋት ነው ያሳመነ ሳይንቲስት ነው።
ይህ ሳይንስ በአሜሪካ በ32 ግዛቶች ተቀባይነት አግኝቶ ህግ ሆኖ ነበር ( Eugenics laws, particularly those related to forced sterilization, were enacted in 32 U.S. states during the early to mid-20th century. These laws aimed to prevent certain individuals, deemed “unfit,” from reproducing. The targets of these laws included people with disabilities, mental illnesses, and those from marginalized communities)።
በዚህም ህግ ምክንያት ከ60ሺ በላይ ሰዎች ያለ ፈቃዳቸው የዘር ማስተላለፊያ መስመራቸው ተቆርጧል፤ በኛ ሀገር ቋንቋ ተኮላሽተዋል። ይሄንን እነ ዶ/ር አብይ በእርግጥ እነ Max Weber በፕሮቴስታንት ኢቲክስ በለጸገ በሚሉት ሀገር ነው። ዘር እንዳይተካ የማኮላሸት ህግ የነበራቸው የአሜሪካ ግዛቶች እነዚህ ናቸው። Alabama, Arizona, Arkansas, California, Colorado, Connecticut, Delaware, Florida, Georgia, Idaho, Illinois, Indiana. Iowa, Kansas, Kentucky, Louisiana, Maryland, Massachusetts, Michigan, Minnesota, Mississippi, Missouri, Montana, Nebraska, Nevada, New Hampshire, New Jersey, New Mexico, North Carolina, Ohio, Oklahoma, Oregon ናቸው።
ይህ እሳቤ ዛሬ እኛ ሀገር ደርሶ የሚሞገሰው ማክስ ዌበር (Max Weber) በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ይሄንን ደካማ ዘረ መል ማጥፋት ትክክል እንደሆ ነው። “Many modernist protestand minster also publicly advocated these laws, endorsing them as an effective means or eliminating white degeneracy, enhancing God;s kingdom on earth”, Leif C. Tornquist,
ሂትለር ሳይንቲስቶቹን ወደ ከካሊፎርያ ልኮ ነው ልምድ የቀሰመው። “ዘር ይበክላል” ያለውን 6 ሚሊዮን ይሁዲ፤ ጂፕሲ፤ አይምሮ ህመመተኛ ሲያጠፋው። ጥቁሮችን ደግሞ ልጅ እንዳይወልዱ በግድ ሆስፒታል እየተወሰዱ ያለ ማደንዘዣ እንዲኮላሹ ይደረጉና የተኮላሹበትን ሰርቲፊኬት ተሰጥቶ ይለቀቁ ነበር። በኑረንበርግ ህግ ደግሞ የጥቁርና የጀርመን መጋባትም ግንኙንተ መፈጸም በህግ የታገደ ነበር። “When the Nazis came to power, one of the first directives was aimed at mixed-race children. Underlining Hitler’s obsession with racial purity, by 1937 every identified mixed-race child in the Rhineland had been forcibly sterilised (ተሎላሸ), in order to prevent further ‘race polluting’, as Hitler termed it. (Holocaust Memorial Day Trust)
አሁን አበሻ ዛሬ ቪዛ አስመትቶ አሜሪካ ልጅ ለመውለድ ይሄዳል። ጀርመን ልጅ ይወልዳለ። ይህ ህግ በሂትለር ጭካኔ ባይተው ኖሮ የሰባት ቀን ግርዘት ሳይሆን የሰባት ቀን ማኮላሸት ይሆን ነበር።
እንስዚህ ሁሉ ህጎች ለምን መጡ ላልን? ምክንያቱ የነጩ ዘር ጥቁሮች በዝግመተ ለውጥ ጥሏቸው ስለሄደ ጥቁሩ ጭንቅላት አላደገም ብለው እራሳቸውን ስላሳመኑ ነው። የጥቁሩ ጭንቅላት ምናባዊ ሀሳብ (abstract knowledge) መያዝ አይችልም በማለት ነው። እነዚህ ምናባዊ እውቀቶች እንደ ሂሳብ፤ ስነ ጽሁፍ፤ ፍልስፍና፤ ሳይንስ ማለት ነው። አንድ ፍጡር ምናባዊ ጽንሰ ሀሳብ መያዝ ካልቻለ አራት ሲካፈል በሶስት ብትለው ሊገባው አይችልም። ወይንም የጸጋዬ ገብረ መድህንን “ጴጥሮስ በዛች ሰዓት” ለአንድ ዝንጀሮ ብታነብለት እንባው ቅርር አይልም።
መጀመሪያ ዳርዊን እንዴት በሁለት መጽሃፍት ዓለምን ያሳመነባቸውን ዐረፍተ ነገሮች እንጥቀስ። እኔም የማጋንን እንዳይመስላችሁ ድርዊን የጻፈውን ሙሉ የእንግሊዘኛውን እናንብብ።
1ኛ፡ “How little can the hard-worked wife of a degraded Australian savage, who uses hardly any abstract words and cannot count above four, exert her self-consciousness, or reflect on the nature of her own existence” Charles Darwin, “The Descent of Man” Chapter VII (7), page 62”
ትርጓሜው ”እንዴት ምንም ምናባዊ ቃላት የማታውቅ፤ ከዐራትም በላይ ቁጥር መቁጠር የማትችል የአንድ የአውስትራልያ አረመኔ ሚስት፡ ስለራሷ ህሊና እና በህይወት ስለመኖሯ ልታስብ ወይንም ልታውቅ ትችላለች?” ነበር ያለው።
2ኛ፡ “The variations, however slight, in the intellectual faculties between a man and the higher animals, especially the apes, are less, than those between one of the lowest savages, such as the Fuegians, or an Australian, and one of the higher races of man, such as the Caucasian.” Charles Darwin “The Descent of Man, and Selection in Relation to Sex.” Chapter VII (7), page 200
ይህ ማለት “በዝንጀሮዎችና በጥቁሮች መሀከል ያለው የአይምሮ እድገት ልዩነት ትንሽ ሲሆን በነጭና በአረመኔ መሀከል ያለው ልዩነት በጣም የሰፋ ነው። በትክክል የተረጎምኩት አይመስለኝም። እናትተው ተርጉማችሁ ተረዱት
3ኛ “At some future period, not very distant as measured by centuries, the civilised races of man will almost certainly exterminate, and replace the savage races throughout the world”. Charles Darwin, “The Descent of Man” 1871, ገጽ 71
በቅርብ ግዜ ብዙ ምዕተ ዓመት ሳይወስድ የሰለጠነው ዘር በእርግጠኝነት ይሄንን አረመኔ (ጥቁሩን) ዘር ያጠፋዋል።
4ኛ “The Western nations of Europe, who now so immeasurably surpass their former savage progenitors, stand at the summit of civilization.”
በምዕራብ አውሮፓ የሚኖረው ነጭ በትልቅ ልዮነት ይሄንን አረመኔ (ጥቁር) ጥሎት ሄዶ ከጋራው ጫፍ ላይ ይገኛል።
5ኛ. “I do not pretend that the remark in my text is more than a statement in certain tribes of mankind, the weak and sickly are left to perish, and that the stronger alone survive.”
እኔ በጽሁፌ ላይ መዋሸት ወይንም መሸፋፈን አልፈልግም። በእርግጠኝነት የምነግራችሁ እነዚህ ደካማ ብሄር ብሄረሰቦች መጥፋታቸው አይቀሬ ሲሆን ጠንካራው ደግሞ ይበራከታል።
ለዚህ ዋነኛ አመክዮ ሆኖ የቀረበው ነየረበው ሀርበርት ስፔንሰር “ጠንካራው ይራባል ደካማው ይጠፋል” (Herbert Spencer “survival of the fittest”)። ይህ ማለት በአእምሮ ጠንካራ የሆነው የነጩ ዘር ከዝንጀሮ ትንሽ ሻል ያለውን ጥቁሩን ማጥፋቱና ምድርን መውረሱ አይቀሬ ነው። ለዚህ ነው 125 ሚሊዮን በላይ ቀይ ህንዶች የተገደሉት፤ የአውስትራልያ፥ የሰሜን አሜሪካ አበርጂኒሶች ሊጠፉ የደረሱት፤ ከ85 ሚሊዮን አፍሪካዊ መሀከል 12 ሚሊዮኑ ታድኖ በባርነት ተጭኖ ወደ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ ሸንኮራ እንዲቆርጥ፤ ጥጥ እንዲለቅም የተወሰደው። ከሁለት ሚሊዮን በላይ አፍሪካዊ በመርከብ ሲጓጓዙ ሞተው ወደ ባህር የተጣሉት።
አንድ ነገር ልጨምርና ወደ ነገሬ ዋናው ነገር ልግባ። ፈረንጆቹ የነ ዳርዊን እሳቤ ግራ እንዳያጋባው የጀርመኑ ሄክል Heackle (1868) የሰውንና የዝንጀሮ ዘራሮችን ዘርዝሮ በስዕል አሳትሟል።
እኔ; እናንተን እና የኛ ጠቅላይ ሚኒስቴራችም; ብልጽናዎችም፤ እነ ዶ/ር ብርሀኑም ምድባችን በቁጥር 6 ነው፤ ቁጥር 7 አያታችን ዝንጀሮ ፎቶግራፍ ነው፦)
ታድያ ይህ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት እና ከጠ/ሚ አብይ ንቀት ጋር ምን አገናኘው ትሉ ይሆናል። ትንሽ ታገሱ። በዚህ እሳቤ ላይ እንዴት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የእውቀት ክምችት ተጠቅሶ ከዝንጀሮነት ወደ ሰውነት እንደተሸጋፈርን ልጥቀስ።
በቻርልስ ዳርዊን ጥቁሮች ምናባዊ እውቀት መያዝ የሚያስችል ጭንቅላት ገና አላገኙም ብሎ ዓለምን ስላሳመነ ነው። የዚህ ዕሳቤ ሰለባ የሆኑ እኛም ሀገር አሉ። ለምሳሌ አቶ መለስ ዜናዊም ከዝግመተ ለውጥ የተቀዳውን ብሄር ባርባርያን እና ሳቬጅ በህገመንግስት አስገቡተው ዛሬም ትግራይ፥ አማራ እና ኦሮሞ የሰለጠነ ብሄር ሲባሉ ደቡብን ምሉዕ ሰው አረመኔ ብለው መድበው ሕገ መንግሥት አጸደቁ። ይሁንና ዶሮን ሲያታልሏት በመጨኛ ጣሏት እንዲሉ በዓመት የብሔር፥ ብሔረ ሰቦችና ሕዝቦች የእኩልነት መገለጫ በዓል ተብሎ መስቀል አደባባይ ሲያስጨፍራቸው ይውሉ ነበር። በህገመንግስቱ እንግዲስህ ሲዳማ፤ ስልጤ፤ ወራቤ ወዘተ ገና ዝግመተ ለውጡን ያልጨረሰ ወደፊት ወደ ብሄርነት እንደ አማራ፤ ኦሮሞና ትግሬ የሚሆኑ ናቸው። የሚያስቀው ደግሞ ምንም ያላነበቡ እንደ አቶ ሬዲዋን ሁሴን ያሉ ይሄንን ህገመንግስት ደምስራቸው እስኪገተር ሲከላከሉ ይችላሉ። በምን መመዘና ነው እኛ ብሄር አይደላችሁም የተባልነው ብለው አልጠየቁም። ጊዜ ያለው የ Sir Edward Taylor መጽሀፍ Primitive Culture ያንብብ።
ዳርዊንና የኢዮጵያ ኦርቶዶክስ
ችግሩ ቻርልስ ዳርዊን ኢትዮጵያ አልመጣም ወይንም ስለ ኢትዮጵያ አላነበበም ለማለት ይከብዳል። ይመስለኛል የሱን ሀተታ የሚያፈርስበት ስለመሰልው መጥቀስ አልፈለገም። ለምን ካላችሁ የሳሙኤል ጆንሰን Samuel Johnson “Rasselas, Prince of Abyssinia” 1759 አሳትሞ በስፋት በእንግሊዝ ተነቧል። ይህ መጽሀፍ እስከ መንኮራኩር ብስክሌት ለመስራት እየሞከረ የነበረ የልኡል ራሴ ላስ ኢትዮጵያዊ አናጺ ታሪክ አለበት። ሁለተኛ በዳርዊን የመጀመሪያ (1857) እና ሁለተኛ መጽሀፍ (1871) ህትመት መሀከል ነው የጀነራል ናፒር ጦር አጼ ቴዎድሮስን ሊወጋ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው (1867/8)። አንድ የጥቁር ንጉስ መድፍ መስራት ፈልጎ እንግሊዞቹን እንዳሰረ አምባሳደሮቹም ፓርላማውም ሲወያይበት ጋዜጦችም ሲጽፉበት ነበር። ከዛ አልፎ የኢትዮጵያውያን መጽሀፍት፤ ዘውድ፤ ስዕሎች፤ አልባሳት፤ የጦር መሳሪያዎች በለንደን ላይ ሲታዮ ነበር። እነዚህ አእምሮው ምናባዊ ሀሳብ መሸከም በማይችል ዝንጀሮ የተጻፉ መጽሀፍት ነው ብሎ ለማመን ይከብደዋል። ስለዚህ አቦርጂኒሶችን ጠቅሶ እንደ ኢትዮጵያ ያለውን የጥቁር ሀገር መረጃ መጥቀስ ሀተታውን ያፈስበት ስለነበረ ተወው።
በእርግጥ ምናባዊ እውቀት የሚይዝ ጭንቅላት የለንምን?
መልሱ “አለን” ነው። ባለፈው አባ ተስፋጽዮን በ1530ዎቹ ወደ ሮም ገብተው የአውሮፓውያንን ምሁራን እንዴት እንዳስተማሩ አይተናል። ሁውመኒስት የሚለውን አስተምህሮ በኢሮፕ መሰረት እንድይዝ እንዳደረጉ ተገጻል። ዛሬ ደግሞ ዋነኛው ምናብ ያስፈልገዋል የሚባለውን የፍልስፍና ትምህርት ቀርሞ በኢትዮጵያ እንደተጀመረ እንይ። በእርግጥ ፍልስፍና የሚይዝ ጭንቅላት ብቻ ሳይሆን ከአውሮፓ ቀድሞ ምክናያታዊነት (Rationalism) የሚባለውን ሀተታ መጀመሪያ የጻፈው ኢትዮጵያዊው ቄስ ዘርያቆብ ነው።
የኢትዮጵያ ፍልስፍና መሰረቱ “ሰው በአርአያ ስላሴ አምሳልና ተፈጠረ ክቡር ፍጡር ነው (ኦሪት ዘፍጥረት 1፥26)። ሲፈጣሪውም ሁሉን ማሰብ የሚያስችል አይምሮና ህሊና ተሰጥቶት የተፈጠረ እኩል ሰው ነው ከሚል ነው። የዝግመተ ለውጥ ሀተታ ደግሞ ሁሉም ሰው እኩል ተፈጠረ የሚለውን አይቀበለውም።
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።”) ከፈጣሪውም ሁሉን ማሰብ የሚያስችል አእምሮና ህሊና ተሰጥቶት የተፈጠረ እኩል ሰው ነው ከሚል ነው። መግዛትና መንዳት ለሰው በሌሎች ፍጥረት ላይ የተሰጠው አንጂ ሰው በሰው ላይ የተሰጠው አይደለም። ስለዚህ ዝግመተ ለውጥ አበላላጭ ነው። ከጥቁር ዝንጀሮ እስከ ነጭ ባለ ወርቃማ ቀለም ጸጉርና ሰማያዊ አይን በመደርደር ያበላልጣል።
ዝግመተ ለውጥ በምን ተረታ?
መረጃው እኛው ሀገር ቢኖርም የኛን የግዕዝ መጽሀፍ አንብበው ተርጉመን የሚነግሩን ፈረንጆቹ ናቸው። ለምሳሌ የዘርዐያዕቆብ የፍልስፍና ትርክት የሚጀምረው በ1852 አንድ የካቶሊክ መኖክሴ ከኢትዮጵያ ጋራዎች ላይ ካሉ ቤተክርስቲያን አገኘሁት ብሎ አስተዋወቀው። ጽሁፏም በዘራያቆብ (1599-1692) በኖረ መኖክሴ የተጻፈ ፍልስፍና ነው።
In 1852, a remarkable manuscript was discovered by a Capuchin monk in the highlands of Ethiopia. The text told of a man named Zera Yacob (1599-1692),
ይሁንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት በርካታ ምናባዊ ጽሁፎችን ስትጽፍና ስታስተምር እንደኖረች የሚያሳይ ነው። ዳርዊን መጽሀፍ ከመጻፉ 304 ዓመታት በፊት ዘረያቆብ የሚባለው ኢትዮጵያዊው ፈልሳስፋ የራሱ ሀተታ ጽፎ ነበር። ይህንን በግዕዝ የተጻፈ የፍልስፍና መጽሀፍ በፈረንጅ የፍልስፍና ዲግሪ የተመረቁት እነ ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ፤ እነ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ሳያነቡት ነው። ይሄንን አንብቦ ወደ እንግሊዘኛ ተርጉሞ አለም ያስማ አፍሪካውያን ፍልስፍና አባት የተባሉት የከካናዳ ዜጋ የሆኑት ፕሮፌሰር ክላውድ ሱምነር ናቸው (Claude Sumner)። የዘርያቆብን ሀተታ ተርጉመው አረ ኢትዮጵያውያን የረቀቀ ፍልስችና ነበራቸው ብለው ለአለም መሰከሩ። ፕሮፌሰር ሰምነር ከነ ሄግል ቀድመው ስለ ምክናታዊነት የጻፈውዘራያቆብ ነው አሉ።
ዘሬ ኢትዮጵያውያን ከኢሮፕያውያኑ ቀድመው ስለ ምክናታዊነው (Rationalism: importance of reason and rational inquiry)፤ ስለ እግዚአብሄር መኖር በምክንያት (Existence of God)። እንደውም ብዙውን ፈላስፋ ያስገረመው የሰውን መሻሻል የእግዚአብሄር ፈቃድ ጭምር ነው በማለቱ ነው። ይህም ቃል። “እግዚአብሄር ሰውን ምሉዕ አድርጎ ሊፈጥረው ሲችል በራሱ ጥረት ወደ ምሉዕነት እንዲሄድ ፈቀደ እንጂ” የሚለው ሀተታው የያዘ ነው። “God could have created a perfect being instead he wanted him to progress to perfection through his own effort” (Sumner, Claude (Trans.). (1976). The African Philosophy of Zera Yacob. Addis Ababa: Addis Ababa University Press.),
ዘረ ያቆብ ስለ ሞራል ፍልስፍና (Moral Philosophy: compassion, justice, and respect) የስነምግባር መሰረት fundamental ethical principles) ናቸው ብሎ መስክሯል። ስለ እኩልነትና ሰብአዊ መብት (Equality and Human Rights) ስለ ጾታ እኩልነት፤ ስለ ባርነት ተቃውሞ፤ ስለ የሰው ልጆች እኩልነት እና ስለ ሀይማኖት መቻቸውል ቀድሞ የጻፈ ነው( religious tolerance and intellectual pluralism through reason and evidence)። ይህ የቄስ ወይንም መነኩሴ ከእንግሊዙ ኦክስፎርድ ወይንም ከአሜሪካው ፕሪንስተን ዮኒቨርስቲ ፒኤችዲ የተሰጠው አይደለም። በኢትዮጵያ የትምህርት ስርአት ውስጥ ያደገ የምናባዊ ሀሳብ ሰው ነው።
እኔ ይህንን የምጽፈው ለጉራ አይደለም እውነታው እድሜ ለጉግል ማንኛውም ስወ በቀላሉ ዘርያ ያቆብ እና ወልደ ህይወት (1667) ሀተታዎች ከሄግል Friedrich Hegel (1807) ከአንድ 140 ዓመት ቀድመው ነው የጻፏት። እኛ በደርግ ግዜ ዮንቨርስቲ የገባነው ሁሉም ተማሪ በግድ (Dialectical Materialism) የሚባል ኮርስ አንደኛ አመት መውሰድ በግድ ይማር ነበር። በዛ ላይ ማርክስ እንዲህ አለ ሄግል እንዲህ አለ ነበር ትምህርቱ ሁሉ። ይሁንና ቆይ አንድ ግዜ ከሄግል ጋር ተመሳሳይ ሀሳብ ያለው የኢትዮጵያ ዘረ ያቆብ የሚባል ፈላስፋ ነበር ያለን አስተማርዎች አልነበረንም። የኔ አስተማሪ ሸዋፈራሁ ይባል ነበር። በግዜው ብዙ ተማሪ የሚከታተለው ፔሌ የሚባል የፍልስፍና አስተማሪ ነበር። ዶ/ር መሳይ ከበደም እዛው ነበር።
ወደ ዳርዊን ስንመለስ ዳርዊን አያቶቻችሁ ዝንጀሮዎ ነበሩ ብቻ ሳይሆን አሁንም ዝንጀሮዎች ናችሁ ነው ያለው፤ በቅርብም ትጠፋላችሁ ነው ብሎ የጻፈው። ለዚህም ዋነኛ መከራከሪያው የጥቁር ጭንቅላት ምናባዊ ሀሳብ መያዝ አይችሉም ብሎ ስላሳመነ ነው። ታድያ እንደ ዘርያቆብ ያሉ ሀተታዎች የጥቁርን ጥልቅ የምናባዊ እሳቤዎች ማሳያ ማረጋገጫ ስለተደረጉ ጥቁሩ ህዝብ ያለ ሞግዚት እራሱን ማስተዳደር ይችላል የተባለው።
በዚህ ላይ ዝርዝር ጽሁፍ የዛሬ ሁለት አመት በተከበረው የአድዋ በአል ላይ አድዋ ሰው አደረገን ብዬ የጻፍኩት ከሪፓርተር ጋዜጣ ላይ አንብቡ። https://www.ethiopianreporter.com/116426/
ዳርዊንን መቼም ሄዶ የሚያነብ ሰው ያለ አይመስለኝም ስለዚህ በዳርዊን ሀተታ ላይ ትችት ያሳተመው የሪቻርድ ዊካርት መጽሀፍን ማንበብ በቂ ነው። መጽሀፏም “From Darwin to Hitler: Evolutionary Ethics, Eugenics and Racism in Germany፣ 2004 R. Weikart
የኦርቶዶክስ አስተዋጻኦ ለፍልስፍና
ከላይ እንዳየነው ዋነኛው የጥቆርን ምሉዕ ሰውነት የሚያጣጥሉ የነበሩት ጥቁሩ አላደገም የሚሉት በስነጽሁፍ የተደገፈ ትርክት መተው አለ መቻሉ ነው። ይህ በኢትዮጵያ የተከማቸው ከ300 ሺ በላይ የሚሆኑት መጽሀፍት በመኖራቸው ነው። እነዚህ መጽሀፎች የጽሎት (Theology) መጽሀፍት ብቻ አይደሉም። መጽሀፎቹ የታሪክ (History)፤ ገድል (Biography) ስነ እጽዋት (Botany)፡ ስነ ከዋክብት (Astronomy): ስነ ህክምና (medicine)፡ ስነ ቀመር (Binary mathematics): ፍልስፍና (philosophy)፡ ስዕል (Painting)፤ እደ ጥበብ (Arts and Crafts): ቀለምና ማዘጋጀት (Chemistry): ሙዚቃ (Music)፡ መድሀኒት መቀመም (pharmacology) ውዝዋዜ (choreography)፡ ስነጽሁድ (Literature): ኮኮብ ቆጠራ (numerology)፡ አርምሞ (meditation); ቋንቋ (ግዕዝ አረብኛ፤ ግሪክ፤ ላቲን) (Languge)፤ ትርጉም (translation) እና የፍልስፍና (Philosopy) ወዘተ ናቸው።
ታድያ ይህ የረቀቀ የፍልስፍና መጽሀፍ ከየት መጣ? ለኛ ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ህዝብ ሁሉ ከዝንጀሮነት ወደ ሰውነት መሸጋገር ማመሳከሪያ ሆኖ የሚቀርበው። ሌላው አፍሪካዊ ፊደል መፍጠር ስለተጫለ በርካታ እውቀቱ አልተመዘገበም ይህ ያሳዝናለ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከ300 ሺ በላይ ጽፋለች። አንድ ቀን ሌሎት ፈረንጆች ግዕዙን አንብበው ሌላ የሚያስደምም ፍልስፍና ይነግሩን ነበር።
ዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምን አበረከተች ማለት ትልቅ የማንበብ አቅም ማጣት ተብሎ የሚመዘገብ ነው። ለዚህ ነው በህግ አምላክ ያለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ፤ ያለ እስልምናና ከሁለቱ ቀድሞ የነበረው የይሁዳ እምነት አስተምህሮና ስነጽሁድ ሁላችንም በመርከብ ተጭነን ብራዚልና በኩባ ሸንኮራ ነበር የምቆርጠው። ስለዚህ ስለ ራሳችን ያለን ንቀትና ጥላቻ እና የፈረንጅ አምልኮ ለሀገር እድገት ምንም አይጠቅምም።
ከጥጥ ለቀማና ከሸንኮራ ቆረጣ ያዳኑንን ቤተ እምነቶች እናክብር። እነዙህ ተቋማት ናቸው የሉአላዊት ሀገር የሰጡን። ያለ ሉአላዊነት ሀገር ደርሞ የጠቅላይ ሚኒስቴር የሚባል ይሰራ መስክ አይኖርም ነበር። ስለዚህ ጳጳሶቹና ሼኮቹ ለዚህ ማበሻቀጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይቅርታ ይጠይቁ የሚል መግለጫ እስኪያወጡ የኢትዮጵያ የክርስትናና የእስልምና መዕመናን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይቀርታ እንዲጠይቁ ግፊት ማድረት የታሪኩም የሀይማኖቱም ግዴታቸው ነው።
ለዚህ ነው እንዲህ አይነት ትልቅ ስህተት ሲሰራ በህግ አምላክ ማለት ያለብን? በክፍል ሶስት በሌላ ጽሁፍ እመለሳለሁ።
አመሰግናለሁ።