Asres Mare Damte

በኦሮምያ ክልል ሰሜን ሸዋ አካባቢ በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የተፈፀመውን ነውረኛ ድርጊት እናወግዛለን!

በሞት አፋፍ ላይ ያለ ስርዓት የሚፈፅመውን አረመኔያዊ ድርጊት ህዝባችን አምርሮ ሊታገለው ይገባል።
የዐቢይ አሕመድ የጥፋት አገዛዝ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ ሲያሻው በተመሳሳይ ሰዓት ሲፈልግ ደግሞ በፈረቃ ጅምላ ግድያና እልቂትን እየፈፀመ ቀጥሏል፡፡ አገዛዙ የከፈተውን ጦርነት ማሸነፍና መቋቋም ሲያቅተው አንዱ ሌላውን የገደለ ለማስመሰል ሲቀሰቅስ፣ ንፁሃንን ሲገድልና በእሳት ጭምር ከነነፍሳቸው ሲያቃጥል አሳይቶናል፡፡
የአማራን ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ደም ለማቃባትና በጥርጣሬ እንዲተያይ ለማድረግ የሚፈጽማቸው ግፎች በቀጠሉበት በዚህ ወቅት በኦሮምያ ክልል ሰሜን ሸዋ አካባቢ አሰቃቂ ግድያዎች ተፈጽመዋል፡፡ ይህንን ድርጊትም ፈፅሞ እናወግዛለን። ይሄን ማውገዝ እንኳን እንደኛ ካለ በደል እና መገደል አንገሽግሾት ለነፃነት ከወጣ ታጋይ ብቻ ሳይሆን
ከማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር የሚጠበቅ ነው።
መሰል ግድያዎችን በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎችም ሆነ በአማራ ክልል ሲፈጽም የሚታወቀውም ሆነ አሰቃቂ ጅምላ ጭፈጨፋዎችን ሲያካሂድ በዓለም ጭምር ሲወገዝ የነበረው የብልጽግናው አገዛዝ ወንድም ከሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ጋር ሕዝባችንን ለመነጠል በማሰብ ይህንን ነውረኛ ተግባር መፈፀሙን መጠራጠር አያስፈልግም፡፡
በመሆኑም:-
1/ አለም አቀፍ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ይህንን ነውረኛ ተግባርና አሰቃቂ ወንጀል እንዲመረምረው እንጠይቃለን፡፡
የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶችም አስፈላጊውን ሁሉ እንድታደርጉ ጥሪ እናስተላልፋለን፤
2/ ሌሎች ኢትዮጵያዊያንም የአገዛዙን ሴራ ተረድተዉ መሰል ድርጊቶችን እንዲያወግዙ እና በመሰል ሴረኛ መንገድ ሕዝቦችን ለማጫረስ የቆረጠውን አገዛዝ እንዲታገሉት ጥሪ እናቀርባለን፡፡
3/ እንዲህ ያሉ አሰቃቂ ግድያዎች የሚያቆሙበት፣ ኢትዮጵያዊያን በተለመደው ወንድማማችነታቸው የሚኖሩበት አገር ለመፍጠር የምንታገለው እኛ የፋኖ ኃይሎች ይህንን ድርጊት የምናወግዘውና በምንቆጣጠራቸው ግዛቶችም ሆነ በምንሰጣቸው ስምሪቶች መሰል ጥፋት እንዳይፈፀም አበክረን የምንጠነቀቅ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡
4/ በመጨረሻም በጭካኔና ነውረኛ መንገድ አሰቃቂ ግድያ የተፈፀመበት የኦሮሞ ወንድማችን እና ሌሎች በጥይት ተደብድበው ለሞቱት የኦሮሞ ወንድሞቻችን ቤተሰቦች ከልብ መጽናናትን እንመኛለን፡፡
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

5 1 vote
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest

1 Comment
Oldest
Newest Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
ታምሩ
ታምሩ
9 days ago

አለም አቀፍ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ከጌቶቻቸው ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል

1
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x