
ገነት አራጌን የት ነው የሰወራችኋት?
ገነት አራጌ ወሎ መርሳ ተወልዳና በልጅነቷ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ቦሌ ከፍ ያለ የኑሮ ደረጃ ካላቸው ቤተሰቦቿ ጋር ያደገች ወጣት ነች፡፡ ወደ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲም በመግባት በፖለቲካል ሳይንስ የመጀመሪያ ድግሪዋን አግኝታ በኢትዮጵያ የሕግ ማዕከል ሰትሰራ ቆይታለች፡፡
ገና በለጋ ወጣትነቷ የዜግነት ፖለቲካ አራማጅ በመሆን ኢዜማን የተቀላቀለች ሲሆን በነበራት ብቃት በጣም አጭር በሆነ ግዜ በብዙ ድርጅቶች ጥምረት የተፈጠረውን የኢዜማን የወጣቶች ክንፍ እንድትመራ ተመርጣ በብቃት ተወጥታዋለች፡፡
በኋላም ከህወሀት ጋር በነበረው ጦርነት “እኔም የምኒልክ እና የጣይቱ ልጅ ነኝ፣ ደስ እያለኝ የምሞትላት አገር አለችኝ” ! በማለት በበጎ ፈቃደኝነት በመመዝገብ በጋሸና ግንባር በመዝመት ጦርነቱ አስከ ተጠናቀቀበት ግዜ ድረስ በጦርነቱ አኩሪ ተሳትፎ አደርጋለች፡፡
ከጦርነቱም በኋላ የኢዜማ የሴቶች ክፍል ተጠሪ በመሆን የሰራች ሲሆን በወቅቱ ገሀድ እየወጡ የነበሩትን የፓርቲውን ፀረ አማራ አቋሞች በፓርቲው ወስጥ መሞገት የጀመረችበት ግዜም ነው፡፡
ኢዜማ በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ የነበረውን የዘር ፍጅት እና በሚሊዮኖች መፈናቀል፣አላየሁም አልሰማሁም ማለቱን ተከትሎ በፓርቲው የተለያዩ መድረኮች ፓርቲው በተቋቋመበት የዜግነት ፖለቲካ መርህ በመመራት ተገቢውን የአባላት አቋም እንዲያንፀባርቅ ከፍተኛ ግፊት በማድረግ ፊት ለፊት ከተጋፈጡ አመራሮች ገነት ቀዳሚዋ ናት፡፡
ፓርቲውን ለቃ ከወጣች በኋላ ብዙ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ከቀድሞ ደርጅቷ ኢዜማ መሪዎች ይደርሳት እንደነበር በወቅቱ ለቤተሰቦቿ እና ለጓደኞቿ ትናገር ነበር፡፡በ2016 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ በአገዛዙ የፀጥታ ኃይሎች ታስራ ድብደባ እና ስቃይ ተፈፅሞባት ለወራት ከታሰረች በኋላ በዋስ ተለቃም ነበር፡፡
በመጨረሻም በየካቲት 8, 2017 ዓ.ም በዕለተ አርብ ከምሽቱ ሁለት ሰዐት አካባቢ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ከሚገኘው የዘመዶቿ ቤት ቀይ ቦኔት በለበሱ የመከላከያ አባላት ተወስዳ አስከ አሁን ልትገኝ አልቻለችም፡፡
የብልፅግና አገዛዝ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር ተወላጅ ዜጎችን ማሰር ፣ መግደል፣አፍኖ ወስዶ ማሰቃየት እንዲሁም በድሮን መፍጀት የዕለት ተዕለት ስራው ቢሆንም፤ የገነት አራጌን ጉዳይ ለየት የሚያደርገው ግን እስከ አሁን በወጡ መረጃዎች መሰረት በኢዜማው መሪ በብርሀኑ ነጋ ጠቋሚነት እና ግፊት የታፈነች በመሆኑ ነው፡፡
ኢዜማ ፀረ አማራ አቋሙ በገሀድ የታወቀ እና በይፋ የታወጀ ቢሆንም፤ፀረ አማራነቱን በማጋለጥ ጥለውት የወጡ አባላቱን እየጠቆመ በማሳፈን የሚሰራው ስራ ግን የነውረኝነት ጥግ ነው፡፡
ብርሀኑ ነጋ በገነት አራጌ ጉዳይ ከአንተ ወድያ ተጠያቂ እንደማይኖር እወቀው!!
እንፋረድሀለን!!
ገነትን የት አደረሳችኋት???
ከአለምሰገድ