ከፈረሱ አፍ፣ ሕወሃት የፕሪቶሪያን ስምምነት ለምን ፈረመ?
በአበራ ገ/ማርያም
አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የቀድሞ የሕወሃት ቃል አቀባይ፣ የአሁኑ የስምረት ፓርቲ ሰብሳቢና የፌዴሬል መንግስት የምስራቅ አፍሪካ አማካሪ፣ ሰሞኑን The African Report ላይ አንድ አጭር ማብራሪያ መጣጥፍ አስነብቧል።
ጽሁፉ በቅርቡ ከተለያዩ ኃይሎች ከMehdi Hasan Al Jazeera’s Head-to-Head ቃለመጠይቅ ላይ ለደረሰበት ከፍተኛ ትችት ማብራሪያ እንደሆነም አልደበቀም።
አቶ ጌታቸው እራሱን በቃለ መጠየቁ ላይ የደረሰበትን ከፍተኛ ትችት ለመከላከል ሲል፣ እስከ ዛሬ ደብቆት ያቆየውን እውነቱን እንደ ወረደ ዘርግፎታል።
አቶ ጌታቸው ማብራሪያውን የጀመረው የፕሪቶሪያ ስምምነት ለምን እስከ አሁን ድረስ አወዛጋቢ እንደሆነ ለመገንዘብ፣ በምን ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ እንደተፈረመ ምስታወስ ተገቢ ነው በማለት ነበር።
ሕወሃትን ወክለው ወደ ፕሪቶሪያ የሄዱት ለመደራደር ሳይሆን፣ በሕወሃት አመራር በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት፣ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ እንደሆነ አስረግጦ ገልጿል።
ጌታቸው በጊዜው የነበረውን እውነታ እንዲህ ይገልጸዋል፣
“…. When the Tigrayan delegation arrived in Pretoria, it did not come to barter….It came with a stark instruction from the Central Command ….to agree to a cessation of hostilities virtually without preconditions. …Prolonging the war risked political annihilation,….”
የጌታቸው ጽሁፍ ከዋናው ተደራዳሪ ከፈረሱ አፍ መሆኑ ለየት ያደርገዋል እንጂ፣ በጊዜው የተለያዩ ለሕወሃት ቅርበት ያላቸው ግለሰቦች በጉዳዩ ተመሳሳይ ሃሳብ ሰንዝረው ነበር።
ጦርነቱ መጀመሪያ ማለቁን ያበሰረው ጄኔራል ታደሰ ወረደ ሽሬ (ትክክለኛው ምዕራብ ትግራይ) መያዙን በተናገረ ጊዜ ነበር። ብዙም ሳይቆይ ውስጥ አዋቂው የቤት ልጅ Alex De Wall ህወሃት እጅ ከመስጠት ውጪ ሌላ አንዳችም አማራጭ እንደሌለው ቢቢሲ እንግሊዝኛ ላይ ጻፈ።
የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተደረገ በኋላ ስዬ አብርሃ ሕወሃት ከመሞት መሰንበትን መርጦ፣ የተባለውን ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ስምምነቱን እንደፈረመ አስረዳ። ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብሎ በግሉ እንደሚያምን ስዬ ገለጸ። የርዕዮቱ ቴድሮስ ፀጋዬ የፕሪቶሪያ ስምምነት 100% አብይ የፈለገውን ያገኘበት መሆኑን በዝርዝር በንዴትና በቁጭት ዘገበ። ስታሊን ባቅሙ “አይ መሬት ላይ ያለ ሰው” በማለት እንዴት ሕወሃት እንዲህ አይነት አሳፋሪ እጅ የመስጠት ስምምነት ይፈርማል ለሚሉ ደጋፊዎችን ቁጣ ለማብረድ ሞከረ።
ጌታቸው በዚህ ጽሁፍ ከዚህ በላይ ያሉት ግለሰቦች የሰጡትን አስተያየት ነው ያጠናከረው። ለድርድር ሳይሆን፣ ከፖለቲካ ሞት ለመትረፍ ስንል አብይ አድርጉ ያለንን ተቀብለን ለመፈረም የሄድነው ብሎ እውነቱን አፈረጠው።
ኢሳያስም ለዚህ ነበር በትግርኛ ሕወኃትን ሲጥ አድርጌ ከመጨረስ ፕሪቶርያ ስምምነት አጨናገፈኝ ብሎ በአብይ የተበሳጨው። ምናልባትም ኢሳያስን ከአብይ ጋር ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ የከተተውና አሁን ላይ በሁለቱ መካከል ለሚስተዋለው የጦርነት ጉሰማ ምክንያት የሆነው።
ዛሬ መልሶ አብይን ከኢሳያስ ጋር ገጥሞ ሊያስጨንቀው፣ አብይ ሕወሃትን ከፓለቲካ ሞት ያተረፈው፣ በወልቃይት ዙርያ ከአማራው ጋር በማፋጠጥ፣ ስልጣኑን ለማርጋጋት መሆኑ ግልጽ ነው።
ከሬድዋን ሁሴንና ከጌታቸው ረዳ ፍላጎት ውጪ፣ የአወዛጊ ቦታዎች (ወልቃይት/ራያ) ባሉበት ይቆያሉ ስምምነት በፕሪቶርያ ድርድር ላይ እንዲካተት ያደረጉት የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት የዶ/ር ይልቃል ምክትል ዶ/ር ጌታቸው በማንሳታቸው መሆኑ ይታወቃል። ጌታቸውም ይሄን ሃሳብ በጽሁፉ እንዲህ በማለት ያጠናክራል፣
“…..The most sensitive questions – Western Tigray, Raya and the sequencing of federal troop withdrawals – were not ignored, but they were deliberately kept out of the opening gambit. The logic was simple: if talks collapsed, the consequences would be existential….”
ስለዚህ ሕወሃት በደማችን/ በጀግንነታችን ፕሪቶርያ ውልን አዋለድን የሚለው የትግራይ ህዝብን ግራ ለማጋባት የተጠቀመው ተራ የተለመደው የአድዋ ገዢ መደብ ተረት ተረት፣ የቅጥፈት ብራቫዶ ነው።
የፕሪቶሪያ ስምምነት የወያኔ ሙሉ ለሙሉ 100% የመሸነፍ ጠባሳ ታሪክ ነው። ፕሪቶሪያ ወያኔ አብይ ጫማ ስር ተምበርክኮ በቃኝ አይለምደኝም ብሎ የፈረመው ስምምነት ነው።
የሕወሃት ቅጥፈት የተለመደ ነው። በአልጄርስ ስምምነት ባድመን በሄግ ትራይቡናል ውሳኔ አስወስዶ፣ የጦርነቱ ድል በፍርድ ቤትም ተደገመ እንኳን ደስ አላችሁ ብሎ አይን ያወጣ ቅጥፈት የቀጠፈ ድርጅት ነው።
ስብሃት ነጋ መቀሌ ከመመሸጉ በፊት፣ ጦርነት ላይ ምናልባት ከተያዝን ሚስጥር ሳናወጣ ለመሞት ሳይናይድ ይዘን ለመሞት እንዞር ነበር ብሎ እንዳልጎረረ፣ በስተርጅና እንደ አይጥ ከጉድጓድ ውስጥ ተጎትቶ ሲወጣ በቲቪ ተመለክተናል። በእንዲህ አይነት አሳዛዥ ሁኔታ የተማረከ ሰውና ደጋፊዎቹ ዛሬ ብርሃኑ ጁላን ምርኮኛ ቢሉ አያምርባቸውም።
ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ በቅርቡ ያሳተመው “አዙሪት” የሚለው መጽሃፍ ላይ እንደገለጸው፣ ሕወሃት በፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ የፈጣሪውን የሻዕቢያ ተምበርክኮ መለመን ደገመው ይላል። ኢሳያስ ባድመ ተይዞ የኢትዮጵያ ጦር ወደ ኤርትራ ሲገሰግስ፣ ለUN ነጋ ጠባ እየደወለ የኢትዮጵያን ጦር አስመራን እንዳይዝ አስቁሙልኝ፣ ያላችሁትን ሁሉ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ አደርጋለሁ እያለ ነጋ ጠባ ይማጸን ነበር።
የሕወሃት አመራርም ጌታቸው ረዳን የፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ አብይ ያለህን በሙሉ እሺ ብለህ፣ ቅድመ ሁኔታ ሳታስቀምጥ፣ ጦርነቱን አስቁምና ከሞት አትርፈን ብሎ ተማጸነ።
ዱባ በቅል ይስቃል ካልሆነ፣ ከምርኮ ውርደት ለመዳን አንድ እራሱን ያጠፋ ጀግና እንኳን ያላበቀለ ድርጅት፤ ብርሃኑ ጁላን፣ ባጫ ደበሌን፣ አለም እሸት ደግፌን፣ አባ ዱላን፣ ምርኮኛ ብለው ሊያንቋሽሹ የሚችሉበት አንዳችም አሳማኝ ምክንያት ሊኖር አይገባም።
የፕሪቶሪያ ስምምነት ለወያኔ face saving excercise (አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም) ነው። የደርጉ ተወካይ እነ ተስፋዬ ዲንቃ በለንደን ኮንፈረንስ ላይ ድርድሩን አኩርፈው እረግጠው ባይወጡ ኖሮ፣ የፕሪቶሪያ ስምምነት አይነት የማርያም መንገድ ለደርግ ባለስልጣኖች ይፈጠር ነበር።
ባጭሩ የፕሪቶሪያ ስምምነት፣ ሙሉ ለሙሉ ተንበርክኮ የተማረከው የወያኔ ጦርና አመራር፣ ከሞት መትረፊያ የማርያም መንገድ ነው።
Related:
1) A few points on Alex De Wall’s recent interview and article
2) Head to Head: Mehdi Hasan with Getachew Reda