በኢትዮጵያ ምድር ማንም መጤ የለም

በግርማካሳ

ኦነግና ሕወሃት አራት ኪሎ ሲገቡ፣ ስልጣን ሲጨብጡ፣ ኢትዮጵያን በዘርና በጎጣ ነው የሸነሸኑት፡፡ የትግሬ መሬት፣ የኦሮሞ መሬት ወዘተ እያሉ፡፡ የትግራይ መሬት ብለው፣ ከጎንደር ክፍለ ሃገር ፣ ከወሎ ክፍለ ሃገር ሰፊ መሬት ነው ወደ ትግራይ ጠቀለሉ፡፡፡ ኦሮሚያ ብለው ሰፊ የኢትዮጵያ ግዛትን ያካተተ ዘረኛና አፓርታይዳዊ መስተዳደር ዘሩጉ፡፡ በትግራይ ህገ መንግስት ትግራይ የትግሬዎች ብቻ ናት፡፡ በኦሮሞያ ሕገ መንግስት ደግሞ ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ብቻ ነው፡፡
የአማራ ክልል ብለው ያነሰች፣ መስተዳደር ሸነሸኑ፡፡ ግን ይህ የአማራ ክልል የአማራዎች ነው አልተባለብም፡፡ የአማራ ክልል የተወሰኑ ኦሮሞዎች ስለሚኖሩ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ብለው ከአማራ ክልል ውስጥ የኦሮሞ ዞን መሰረቱ፡፡ እዚያ ያለውን ህዝብ አማራ አገው ብለው ከፋፍለዉት፣ ሁለት የአገው ዞኖች (አዊ ዞንና ዋገምራ ዞን) ሸነሸኑ፡፡ የአርጎባ ልዩ ወረዳ ብለው ሌላ መስተዳደር ፈጠሩ፡፡ የቅማንት ብለው ሲንቀሳቀሱ ነበር፡፡ በአጭሩ የአማራ ክልል የአማራ ሳይሆን

የብሄር ብሀረሰቦች ክልል ነው ብለው፣ አማራው እንደ ነገደ ከትግሬውና ከኦሮሞ ጋር እንዳይገዳደር አደረጉት፡፡ እንደ ሳንድዊች አድርገው ለመጨፍለቅ፡፡
ትግራይ፣ ኢሮቦች፣ አርጎባዎች፣ አማራዎች ወዘተ ይኖራሉ፡፡ ግን ለነሩስ ልዩ ዞን አልተሰጣቸውም፡፡ አማራ ክልል እንደተደረገው፡፡ ትግራይን የሸነሸኑት ሰሜን፣ ምእራብ፣ ደቡብ ወዘተ እያሉ ነው፡፡ ለምን አላማቸው ታላቋ ትግራይ ለመመስረት ስለሆነ፣ ለብሄረ ብሂረሰብ መብት ቆመናል እያሉ፣ በትግራይ ውስጥ ሌሎች ብሂረሰቦችን ግን የመጨፍለቅ ፖለቲካ ነው የነበራቸው፡፡ ሁሉም ነገር በትግሬኛ እንዲሆን ተድርጎ፣ ሌሎች በግድ ትግሬዎች ናችሁ ተብለው ከፍተኛ አፈና ሲፈጸምባቸው ነበር፡፡

በኦሮሞ ክልል ያለፈው የሕዝብ ቆጠራ እንደሚለው 15% ኦሮሞ አይደለም፡፡ እውነታው ግን ወደ 25% ኦሮሞ ክልል ውስጥ የሚኖረው ኦሮሞ አይደለም፡፡ ወደ ኦሮሞ ክልል በተጠቃለሉ የሸዋ መሬቶች፣ ከግማሽ በላይ ነዋሪው ኦሮሞ አይደለም፡፡ ለምሳሌ በኦሮሞ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ፣ አዳማ ወረዳ፣ ናዝሬት ከተማ፣ ሎሜ ወረዳ። ቦሰት ወረዳ፣ በኦሮሞ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ቅምብቢት፣ ዴራ አለለቱ፣ ጊምቢቹ፣ ግራር ጃርሶ፣ ወረ ጃርሶ፣ አቢቹና ኤኛ ወረዳዎች ። በወለጋ ኪረሚ፣ አማሩ፣ አቤደንጎሮ ፣ ጃርዴጋ ጃርቴ ወዘተ ወረዳዎች አማራዎች አብላጫ ድምጽ አላቸው፡፡ ግን በነዚህ ቢታዎች በአማርኛ እንዲማሩና በአማርኛ አገለግሎት እንዲያገኙ፣ ልዩ ዞን እንዲሰጣቸው አልተደረገም፡፡
ከ1983 ዓ/ም ጀምሮ የተዘረጋው ስርዓት፣ ወገኖች ጸረ ኢትዮጵያ ስርዓት ነው፡፡ ኢትዮጵያን አፍርሶ፣ ታላቋን ትግራይና ታላቋን ኦሮሚያ ለመገንባት ታስቦ የተዘረጋ ቆሻሻ ስርዓት ነው፡፡ ኢትዮጵያዉያንን ደም ያፋሰሰ ስርዓት ነው፡፡ እንደ አገር አብረን በፍቅር እንዳናድግ ያደረገ ስርዓት ነው፡፡
አሁንም የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ የአማራ፣ወዘተ መሬት የሚለው ቀርቶ፣ “ሁሉም ኢትዮጵያዉያን የኢትዮጵያዉያን ነው፣ ፣ማንም ኢትዮጵያ በፈለገበት ቦታ መኖር፣ መስራት፣ ሃብት ማፍራት፣ መምረጥ፣ መመረጥ መቻል አለበት ” ወደ ሚል ካልመጣን እመኑኝ ከፊታችን የሚጠብቀን የከፋ ነገር ነው፡፡


Opinions expressed by contributors are their own. Ethiofact does not endorse and is not responsible for the accuracy of any of the views expressed in the content on this site.

guest

0 Comments
Oldest
Newest Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments

0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x