Logo

በአዲስ አበባ የንግዱን ማህበረሰብ የማተራመስ እርምጃው ቀጥሏል ተባለ

December 3, 2010

•    ከሻይ ቤት ጀምሮ እያንዳንዱ ትንንሽ ነጋዴ የቫት ተመዝጋቢ እንዲሆን አስገዳጅ እርምጃ ተወስዷል፣
•    እያንዳንዱ ነጋዴ የዕለት ሽያጩን የሚመዘግብበት ማሽን በግዳጅ “ሀሮን” ከተባለ አንድ አስመጪ ኩባንያ ብቻ እንዲገዛ ተደርጓል፣
•    የእንዳንዱ ነጋዴ ዕለታዊ የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን በኔትዎርክ ከታክስ ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ጋር እንዲገናኝ ተደርጓል፣

በዚህም መሰረት የነጋዴው ማህበረሰብ ባለፉት ዘመናት አይቶትም ሰምቶትም በማያውቀው ሁኔታ ተወጥሮ በመያዙና የንግድ እንቅስቃሴውንም ሆነ እለታዊ ሽያጩን በመመዝገቡ ሂደት በልምድ ማነስ ምክንያት በሚፈጥረው ስህተት ግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት በሚመሰርትበት ክስ እጅግ መማረሩ ታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ ግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት በየቀበሌው ባቋቋማቸው የስለላ ቃፊሮች (Tax Intelligence) አማካይነት በእያንዳንዷ መንደር በየዕለቱ የምትከፈትና የምትዘጋ የንግድ ተቋምን እንቅስቃሴ ከመከታተል በተጨማሪ እነዚህ የመንግስት ሰላዮች በየሱቁ ገዢ መስለው በመግባት በሚያደርጉት ስለላ ነጋዴዎች መሰላቸታቸውም ይነገራል፡፡

በየቀበሌው የተቋቋሙት እነዚሁ የግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ወኪሎች፤ ሰሞኑን ደግሞ የንግድ ሱቅ ከፍተውና ፈቃድ አውጥተው የሚሰሩ ነጋዴዎችን ብቻ ሳይሆን፣ በየመንገዱ ላይ ሲጋራ፣ ማስቲካና ጨርቃጨርቅ የሚቸረችሩ ሱቅ በደረቴዎችን ጭምር በመመዝገብ ላይ መሆናቸውም ታውቋል፡፡

በአዲሱ የባንክ አሰራር አዋጅ መሰረት በብሔራዊ ባንከ ውስጥ በቀድሞው የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር በአቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራ አንድ የፋይናንስ ኢንተሊጀንስ ዩኒት (Finance Intelligence Unit) ተቋቁሟል፡፡ የዚህም ዩኒት ዋነኛ ተግባር ባለሀብቶች በባንኮች በኩል የሚያደርጉትን የገቢና ወጪ የፋይናንስ ፍሰት መቆጣጠር መሆኑን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ማንኛውም በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ግለሰብም ሆነ ድርጅት የመንግስትን ግብር በመክፈል ህጋዊ ስራ እንዲሰራ ማድረግ ተገቢ መሆኑን በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች ገልጸው፣ “የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች የሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላለፉት ሃያ ዓመታት በህገ-ወጥ መንገድ ሲበለጽጉ መንግስት የት ነበር? የስርዓቱ ደጋፊዎች የሚበቃቸውን ያህል ሀብት ካፈሩ በኋላ ዛሬ ሁላችሁም ወደ ህጋዊ አሰራር በአንድ ጊዜ ግቡ ማለትና በየሰበብ አስባቡ ነጋዴውን ማሳቀቁና ማስበርገጉ ተገቢ አደለም” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የኢህአዴግ መንግስት ነጋዴዎችን ግብር እንዲከፍሉ ከማድረግ ጎን ለጎን በህገወጥ ንግድና የመሬት ወረራ ተሰማርተዋል ያላቸውን ግለሰቦችና ድርጅቶች በዚህ እየተገባደደ ባለው የህዳር ወር በሬዲዮና በቴሌቪዥን በታጀበ ዘመቻ ሲያዋክብ መክረሙ የሚታወቅ ሲሆን፤ መንግስት በመሬት “ወራሪዎች” ላይ ብቻ ሳይወሰን በአራጣ አበዳሪዎች ላይ፣ ህገወጥ የውጭ አገር ገንዘብ ምንዛሬና የሃዋላ ስራ ያከናውናሉ በተባሉ ነጋዴዎች ላይ፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ደርጋሉ በተባሉ አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ግለሰቦች ላይ፣… ተከታታይ ዘመቻ ከፍቷል፡፡

በግቦት ወር 2002 ዓ.ም አገራዊ ምርጫ ከተደረገ ወዲህ፣ መንግስት በንግድ ስራ ላይ በተሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ እንዲህ ዓይነት የማያቋርጥና ተከታታይነት ያለው ዘመቻ የከፈተው ለምንድን ነው? ከዚህ ዘመቻ በስተጀርባ ያለው ፖለቲካዊ አንደምታስ ምን ይሆን? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የፖለቲካ ታዛቢዎች “መንግስት ይህንን ሁሉ የሚያደርገው ነቃ ያለውና መካከለኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ተረጋግቶ እንዳያስብ በማድረግና በሃሳብ፣ በጭንቀትና በራሱ ጉዳይ በመወጠር መንግስትን የሚቃወም ሃሳብ እንዳያቀነቅን ለማድረግ ነው” የሚል ጥቅል አስተያየት በማስቀመጥ ይኸው የማዋከብ፣ ውጥረት የመፍጠርና ፋታ የመንሳት ዘመቻ በቀጣይ ጊዜአትም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማዕከል አድርጎ እንደሚቀጥል የሚጠበቅ ነው በማለት ደምድመዋል፡፡

በመንግስትና በገዢው ፓርቲ በኩል ይህንን መሰል የማያቋርጥ የማዋከብ እርምጃ ሲወሰድ በአገር ውስጥም ይሁን በውጭ አገር ያለ አንድም ተቃዋሚ ፓርቲ አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ አስተያየት ሲሰጥ አለመታየቱ ደግሞ ጉዳዩን ይበልጥ አስገራሚ ብቻ ሳይሆን እንቆቅልሽ አድርጎታል፡፡

Share

6 comments on “በአዲስ አበባ የንግዱን ማህበረሰብ የማተራመስ እርምጃው ቀጥሏል ተባለ

  1. what the government is doing is the right thing. Every one has to do bussiness in a transparent way. We have to support the government on this issue. Ethiopia has been a place where some people do busssines with out paying taxes ….. indirectly making the people more and more poor. We are very happy to see the government taking series actions agoinst those thieves. EPRDF keep the good work UP!!!

  2. The only thing that concern me is that, is the tax calculation transparent and the taxpayers know how it is done. If this is done it will be coruption free,And it will be known liablity to the tax payer in local areas. and is the money collected goes to devlopments fairly to tax payers concerned problems.

  3. And more over i am concerned with the wrighters attitude, I don’t get it what is he/she is trying to address. or his/her intention. Don’t forget we have to pay tax. And we have to use the tax collected to fight against corruption and unlawfull acts. There for its better to keep an eye on the money collected…so as its used for the right purpose…what am saying is that let’s show our people that they have the right to decide about the tax they payed.

  4. There is a saying ‘Wedesh Ketedefash Biregtush Ayikefash’ You gave your votes to EPRDF. You did not help the oppostion parties especially during the election to make it difficult for eprdf to steal the votes. As a result they gained 99.6. Now you should accept the consequence. No need to complain.

  5. Everwhere is tax such as europe,u.s.a sowhat? pay the tax and share the wealthy for infrastructre and development for the country that is the resposibility of everybody to buid the country.good move by eprdf.

  6. Well so along the regime is even handed to all, it is welcome.
    But,how about EPRDF business organisations? Why are they exempt and doing business contrary to the law? You can not have two laws in Ethiopia.

Comments are closed