ሦስተኛ አማራጭ የሌለው “የጥቁርና ነጭ” ፖለቲካችን አባዜ
የሀገራችን ፖለቲካ እጅግ በጎላ መልኩ ጥዋት ማታ ይወቀጣል፡፡ ይሰለቃል። ሲቻል በአደባባይ፣ ሳይቻል በየጓዳው እንደጉድ ይብጠለጠላል። በየመሸታ ቤቱ በወሬ ቱማታ ይበራያል፡፡ ይሁን እንጂ፣ የሚወራለትንና የሚመከርበትን ያህል ውጤቱ ያማረ አልሆነም። ባለመታደል ለፍሬ አልበቃም፡፡ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ አላደገም። ድህነት አልጠፋም። (መጥፋት ቀርቶ አልተቀነሰም) የህዝቡ ሰላምና ደህንነት ከስጋት አልወጣም። ሰብአዊ መብት አልተጠበቀም። መልካም አስተዳደር አልሰፈነም። ከሀገሪቱ የድርቅና ርሃብ ድንኳን አልተነቀለም። “ይኸ ሁሉ የሚሆነው በጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ላይ የተገነባ የፖለቲካ መደላድል ባለመፈጠሩ ነው” በሚለው እሳቤ ብዙዎች ይስማማሉ።
እዚህ ላይ “እኛ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች የዓለም ህዝቦች በተለየ ሁኔታ ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመፍጠር ለዘመናት ቀፍድዶ የያዘንን ችግር መፍታት ያልቻልነው ለምንድን ነው?” የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ይመስለኛል። የዚህ መጣጥፍ ዋነኛ ዓላማም ለዚህ መሰረታዊ ጥያቄ የሚሆን የበኩሌን ምላሽ መፈንጠቅ ይሆናል። ወደ ጥያቄው ባህሪና ወደ ምላሹ ከማምራቴ በፊት ግን ለመንደርደሪያ የሚሆኑ አንዳንድ ታሪካዊ ዳራዎችን መጠቃቀስ አስፈላጊ መስሎ ስለታየኝ በዚህ የጽሑፌ ክፍል በዚሁ ዙሪያ ለማተኮር እወዳለሁ።
እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር ስርዓት የተጀመረው በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት፤ በ1900 ዓ.ም አስራ ሁለቱ ሚኒስትሮች ከተሾሙበት ጊዜ በኋላ መሆኑን የታሪክ ምሁራን ያስረዳሉ፡፡ በአንድ ሀገር ባህላዊም ይሁን ዘመናዊ የመንግስት አወቃቀር ካለ የዚያ መንግስት የስልጣን ተቀናቃኝ የሆነ ኃይል ደግሞ ጎን ለጎን መደራጀቱ አይቀሬ ነው፡፡
በዚህ ረገድ፣ የሀገራችንን የተቃውሞ ፖለቲካ አደረጃጀት ስንመለከት ቀድሞ በነበሩት ዘመናት በቤተ መንግስት አካባቢ ከሚስተዋሉ “የመንግስት ግልበጣ ሴራዎች” (Palace Conspiracy) እና የስልጣን ሽሚያ ውጪ የህዝብን ብሶትና ጥያቄዎች መሰረት ያደረጉ አልነበሩም፡፡ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ የህዝብን ጥያቄ መሰረት ያደረገ የተቃውሞ ንቅናቄ የታየውም በዚሁ በአፄ ምንሊክ ዘመነ መንግስት በተካሄደ የስራ ማቆም አድማ ነው፡፡
በአፄ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት አካባቢያዊ ይዘት ያላቸው የሕዝብ ጥያቄዎችን መሰረት ያደረጉ ጎላ ጎላ ያሉ የተቃቀወሞ ንቅናቄዎች ታይተዋል፡፡ ለአብነት ያህል የራያና አዘቦ አርሶ አደሮች የቀዳማይ ወያኔ ንቅናቄ፣ የጎጃምና የባሌ አርሶ አደሮች አመፅ በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ በሁለቱ ወንድማማቾች ማለትም በመንግስቱ ንዋይ እና በግርማሜ ንዋይ በ1953 ዓ.ም የተካሄደው የመንግስት ግልበጣ ሙከራ፤ በይዘቱ፣ ባነሳቸው ጥያቄዎችም ሆነ በአፈጻጸሙ ቀደም ሲል ከተካሄዱ አካባቢያዊ አመፆች የተለየና አገራዊ ይዘትና የህዝብ ብሶቶችን መሰረት ያደረገ እንደነበር መገንዘብ ይቻላል፡፡
በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ መልክና ቅርፅ ይዞ፣ ዴሞክራሲያዊ የህዝብ ጥያቄዎችን መሰረት አድርጎ መንቀሳቀስ የጀመረው ከዚህ የመፈንቅለ መነግስት ሙከራ በኋላ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች መደራጀትና በሀገራቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየትም መጀመራቸው ይነገራል፡፡ የህዝብ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ያገኙ ዘንድ የስርዓት ለውጥ መምጣት እንዳለበት የለውጥ አንቀሳቃሾቹ እምነት ነበር፡፡
በዚህ ወቅት ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች ከአውሮጳ ቅኝ ገዢዎችና ከኢምፔሪያሊስቶች ነፃ የወጡበት ወቅት ስለነበር በአውሮጳና በአሜሪካ በትምህርት ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወጣት ምሁራንም በአገራቸው አንዳች ዓይነት የስርዓት ለውጥ መደረግ እንዳለበት አምነው መንቀሳቀስ ጀመሩ፡፡ በአገር ቤት ያሉ ወጣት ተማሪዎችም የፊውዳል ስርዓቱ በአርሶ አደሩ ላይ የሚያደርሰውን ግፍና መከራ የማስቆም ኃላፊነት እንዳለባቸው በመገንዘባቸው “መሬት ላራሹ እና የብሔር ጥያቄ” የመሳሰሉ አንጋፋ ሕዝባዊ አጀንዳዎችን አንግበው አደባባይ በመውጣት ቁጣና ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል፡፡
እነዚህ የተቃውሞ ኃይሎች በአፄ ኃ/ስላሴ መንግስት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በተለያዩ መድረኮችና በተለያዩ አጋጣሚዎች ከመግለጽ አልፈው፤ በሀገሪቱ ህጋዊ የፖለቲካ ስራ ለመስራት የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ትርጉም ያለው ይፋዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ አልቻሉም፡፡ ይህም በመሆኑ በህቡዕ ተደራጅተው መንቀሳቀስ ጀመሩ፡፡ በዚህም መሰረት አንዳንዶቹ የሚያሰባስባቸው ርዕዮተ-ዓለም መርጠው፣ አገር አቀፍ ቁመና ይዘው ሲደራጁ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ በአካባቢያዊ አጀንዳዎች ዙሪያ መሰባሰብን መረጡ፡፡ ይሁን እንጂ፣ አደረጃጀታቸው ህቡዕ በመሆኑ ምክንያት አንዱን ቡድን ሌላው ሊያውቀው አልቻለም፡፡ በዚህም የተነሳ ተመሳሳይ አጀንዳ ይዘው ተመሳሳይ ርዕዮተ-ዓለም የሚያቀነቅኑ በርካታ ቡድኖች ሊፈጠሩ ቻሉ፡፡
እነዚህ የፖለቲካ ቡድኖች ተመሳሳይ ጥያቄዎችና አንድ ዓይነት ርዕዮተ-ዓለም ከመከተላቸው አኳያ የሰፋ ልዩነት ስለማይኖራቸው፤ ተቀናጅተው፣ ግንባር ፈጥረው ወይም ተዋህደው መስራት ሲገባቸው፤ መሪዎቻቸው በያዙት ጽንፈኛ አቋም ምክንያት የህዝብ ጥያቄዎችን ወደ ጎን በመተው አንዱ ቡድን ሌላውን ጥሎ አሸናፊ ለመሆን የከፋ ሽኩቻ ውስጥ ገቡ፡፡
በአጠቃላይ፤ ከአፄ ኃ/ስላሴ ስርዓት መውደቂያ ዋዜማ ጀምሮ ብቅ ብቅ ብለው የነበሩት የፖለቲካ ኃይሎች የሀገሪቱን ፖለቲካ «እኔ» እና «ሌሎች» በሚል ሁለት ጎራ ከፍለው «ወይ እኔ ጋር ነህ፣ እኔ ጋር ካልሆንክ እዚያኛው ጎራ ውስጥ ነህ» የሚል ጭፍን አቋምን ይዘው ሌላ ዓይነት የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለምና አማራጭ ፖሊሲ እንደሌለ ድምዳሜ በማስቀመጣቸው የሀገሪቱ ፖለቲካ «ጥቁር» እና «ነጭ» ብቻ እንደሆነ ተደርጎ ተወሰደ፡፡ ሶስተኛም፣ አራተኛም፣… አማራጭ መኖሩ እውቅና ተነፈገው፡፡ (ክፍል ሁለት ይቀጥላል)
ebakih wendime lemin tikebatiraleh? You better keep silent and watch if you don’t understand how the politics is marching in Ethiopia.
Ye temitatabet arfo yikemetal enji aykebatirim.
@ getachew tsehaye, so do u think u know??? ask ur self again. any one who has a better understanding do not condemn others for expressing their opinion.
Getachew, you did not even point out one paragraph that you think is ‘Yetemtata’ Therefore it is you who suffer from some kind of mental problem
Getachew you better go and educate yourself.I think you are not in a position to comment.
To getachew tsehaye,
I think what the writer says is exhibited by your own comment. That is the so called “Black” or “White” politics means. Getachew, you better forward your opinion in a civilized manner! «እኔ ልናገር እናንተ ዝም በሉ» ማለት ነውረኛ የመንግስቱ ዘመን ሰዎች አስተሳሰብ ነው፡፡ ባልሳሳት ጸሐፊውም ያለው ይህንኑ ይመስለኛል፡፡ እናም ጌታቸው፣ ልብስህ ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብህም የሰለጠነ ቢሆን ይመረጣል፡፡ Please grow up getachew!
you comment on derga, Haileslsia and Eprdf But think what do you do yourself in this world before evil comments on those groups? comment is easy but work is diffcult.
you are the enemy of all system that is weird.childish comment.
Getacheu tsehaye . You are on the wrong place. Go to your friends and hear what you want. If you want to learn the reality just keep quite and read .This forum belongs to civilised Ethiopians with modern thinking . Your strategy is already tested and failed.
We know you will repeat the writers opinion but only after ten years.This is what you and the likes doing.
Thank you Dear Mergy Damtew
Keep on doing yor nice job
I know you can change anyting in this world but It is hard to change people mouth an less they dade.
biniam, belete, yigermal,Abba Jihad Muhie, Abe, Roha, fly, minamin minamin…..
Gobez, minew weredachihubign???? Wendim yelachihum ??? Lekso lekso lekso——merdo merdo merdo…edime lik ?!?!?! Min nekachihu !!!!!
Gecho,
This is only to channel you to the right track, because we love you all. Ena Atalkis Eshi?
Aba Muhie, what is your reference for a right truck? Just your love for all? ….but i am afraid it all depends on the circumstance at hand. Like for instance, aend tenegna sew be ebidoch ketema is himself insane/crazy. isn’t that right?
so what is “right truck” as per your dictionary, afkari wedajachin? esti ebakih chewata amta Aba Muhie !!!
Gecho,
This is defocusing. We know where to go, we know our objective, You can’t defocus us!
Aba!
Melkam menged yihunilwo!!!
yegeza tilan eyeterateru, defocus, defocus eyalu guzo mebertat new engdih. …….oho! aha! meshenef yelem!!!