“የነጭና ጥቁር” ፖለቲካችን ስንክሳር ሲበራይ!

በበኩሌ ይህንን ተከታታይ መጣጥፍ ለማቅረብ የተነሳሁት እንደ ገደል ማሚቶ ራሴ ጩኸት አሰምቼ፣ የራሴን ጩኸት በማዳመጥ ልቤን በሀሴት ለመሙላት ሳይሆን፤ የአንባቢን ስሜት ኮርኩሬ ወደ ውይይት መድረክ ለመሳብ በመሆኑ በቀጣይ ጊዜአት የውይይት ሃሳቦችን የያዙ ሰፋፊ አስተያየቶች እንደሚቀርቡ ተስፋ በማድረግ ወደ ዛሬው ርዕሰ ጉዳይ ላምራ!

ለመጀመር ያህል፣ በክፍል አንድ መጣጥፌ መንደርደሪያ ላይ በጥያቄ ምልክት ቋጥሬ ያስቀመጥኩትን ጥያቄ ደግሜ ላንሳ። “እኛ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች የዓለም ህዝቦች በተለየ ሁኔታ ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመፍጠር ለዘመናት ቀፍድዶ የያዘንን ችግር መፍታት ያልቻልነው ለምንድን ነው?” ይላል ጥያቄው። አሁንም በዚህኛው ጽሑፍ የማተኩረው ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሆኑ “መላምቶችን” ለማግኘት በመንደርደሩ ዙሪያ ላይ ይሆናል።

እስከ ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት መገባደጃ ማለትም እስከ ደርግ ስልጣን መያዝ ድረስ በነበረው ጊዜ ገዢዎቹን ለመቃወም ብቅ ብቅ ያሉ የፖለቲካ ኃይሎች (ሁሉም ማለት ይቻላል) የግራ ፖለቲካ አራማጆች ነበሩ። እንደሚታወቀው የግራ ፖለቲካ ደግሞ ከአንድ ጠንካራ ‘የወዛደሩ ፓርቲ’ ውጭ ሌላ ዓይነት ተቀናቃኝ አስተሳሰብ የያዘ ፓርቲ ተፈጥሮ እድል እንዲያገኝ አይፈቅድም።

ይህም በመሆኑ በወቅቱ ተፈጥረው የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ራሳቸውን ብቸኛ ለሀገርና ለሕዝብ ተቆርቋሪና ብቸኛ ለሀገር ቅን አሳቢ አድርገው የመቁጠርና ከእነርሱ ውጭ ያለን አስተሳሰብ ሁሉ ‘አቆርቋዥና አድሃሪ’ አድርገው የመፈረጅ መንገድን ይከተሉ ነበር። በአስተሳሰብ ‘ከእኔ ጋር ከሆንክ መልዐክ፣ ከእነ እንቶኔ ጋር ከሆንክ ጭራቅ ነህ’ የሚል አቋም በማራመድ የሀገሪቱን ፖለቲካ “ነጭ እና ጥቁር” ቀለም ቀብተው ሁለት ጽንፈኛ ጫፎች ላይ አስቀመጡት።

ደርግ ስልጣን ላይ እንደወጣ በነበሩት ጥቂት ዓመታት የፖለቲከኞቹን ፍትጊያ ሲያስተውል ከቆየ በኋላ ሁሉንም ኃይሎች ጨፍልቆ ‘በሀገሪቱ ከእኔ በስተቀር ምንም ዓይነት የፖለቲካ አስተሳሰብን ማራመድ አይቻልም’ አለና በ17 ዓመታት የአገዛዝ ዘመኑ ባወጣቸው አዋጆች ጭምር “ያሰበ፣ ለማሰብ ያሰበ ወይም አስቦ የተገኘ፣…” የሚሉ አገላለፆችን በመጠቀም ‘ኢሠፓ’ የተሰኘ አንድና ብቸኛ ፓርቲ (Dominant Party) አቋቁሞ የአገዛዝ ዘመኑን በማጠናከሩ በሀገሪቱ ሁለተኛም፣ ሶስተኛም፣… አማራጭ የፖለቲካ አስተሳሰብ ስለመኖሩ እንኳ ግንዛቤ ያለው ሰው እንዳይኖር አደረገ።

ደርግ ወድቆ ኢህአዴግ ሀገሪቱን ማስተዳደር ሲጀምር “ጠመንጃ አታንሱ እንጂ የፖለቲካ ድርጅት አቋቁማችሁ የፈለጋችሁትን ርዕዮተ-ዓለም በማራመድ እኔንም ጭምር መፎካከር ትችላላችሁ” በሚል መንፈስ መድረኩን ክፍት አደረገው፡፡ ኢህአዴግ በሀገሪቱ የሁሉም ነገር መለኪያ መስፈሪያው “ዘር፣ ጎሳ፣ ብሔር፣…” እንዲሆን በነበረው (አሁንም ባለው) አቋሙ የፖለቲካ አደረጃጀቱ ርዕዮተ-ዓለምን ሳይሆን “ጎሳን/ዘርን” መሰረት አድርጎ ይዋቀር ጀመር፡፡

ይሁን እንጂ፣ በአንድ ብሔር/ጎሳ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ዓይነት የፖለቲካ አመለካከት ሊኖራቸው ባለመቻሉ ትንንሽ የሕዝብ ቁጥር ያላቸው “ህዳጣን ጎሳዎች” ሳይቀሩ ከአንድ በላይ ፓርቲ ተመሰረተላቸው፡፡ የዘር አደረጃጀቱ ቀደም ሲል ከነበረው “ወይ እኔ ጋር ነህ፤ እኔ ጋር ካለሆንክ እነ እንቶኔ ጋር ነህ” ከሚለው “የነጭ እና ጥቁር” የፍረጃ አስተሳሰብ ጋር ሲቀየጥ፣ የሀገሪቱ ፖለቲካ ዓይነቱ እንደጠፋበት ልቃቂት ይበልጥ ተወሳሰበ፡፡

ብቅ ብቅ ያሉት የፖለቲካ ኃይሎች፣ እንደ መሪ (Leader) ሕዝቡን የሚመሩበት የጠራና የነጠረ ርዕዮተ-ዓለም ስላልነበራቸው፣ ከመጯጯህ የዘለለ ስራ ሰርተው የዴሞክራሲ ስርዓት መመስረት አልቻሉም፡፡ ሕዝቡም ፖለቲከኞቹ ማዶ ለማዶ ሆነው የሚወራወሯቸውን የቃላት እሩምታ እያዳመጠ፣ ለዘመናት የሚመኘውን የዴሞክራሲ ስርዓት እያለመ በዝምታ መደመሙን ቀጠለ፡፡

በዚህ የሕዝብ ዝምታና የጎሳ ፖለቲከኞች ቱማታ መሀል ህብረ-ብሔራዊ አደረጃጀትን መሰረት ያደረገና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እታገላለሁ የሚል “ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ህብረት (ብዴህ)” የተሰኘ ፓርቲ ድንገት ብቅ አለ፡፡ ሕዝቡም በዚህ ፓርቲ ዙሪያ በመሰባሰብ ለአገር አቀፍ (ህብረ-ብሔራዊ) ፓርቲ ያለውን ድጋፍ በመግለጽ፣ በአንጻሩ ለጎሳ አደረጃጀት ያለውን ተቃውሞ ገለጸ፡፡

ነገር ግን፣ ይህ ሕብረ-ብሔራዊ አደረጃጀት ያለው ፓርቲ የሕዝቡን ስሜትና ፍላጎት በጥበብና በትእግስት በመግራት ወደሚፈለገው አቅጣጫ በመምራት ለውጤት ማብቃት ሲገባው፤ አበው “የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት…” እንዲሉ፣ የህዝብን ከመለኪያ በላይ ያፈተለከ ስሜት ተከትሎ በመንጎዱ ኢህአዴግ ያዘጋጀለት ወጥመድ ውስጥ ሰተት ብሎ ገብቶ እስከ መጨረሻው አሸለበ፡፡

ከዚህ ጊዜ በኋላ መጯጯሁ ቀጠለ፡፡ የሀገሪቱም የፖለቲካ ትኩሳት እየተጋጋመ ቀጠለ፡፡ የኢህአዴግም አምባገነናዊ ጉልበት በመንግስታዊ አቅም እየጎለበተ መፈርጠሙን ቀጠለ፡፡ እናም፤ እንኳን ሌሎች የደረሱበት ደረጃ ልንደርስ፣ እንኳን አማራጭ ፖሊሲዎችን ልናገኝ፣ እንኳን የሰለጠነ የዴሞክራሲ ስርዓት ልንገነባ፣ ኢህአዴግ ስልጣን ሲይዝ የታዩት ጭላንጭሎችም ጭራሹኑ ጨልመው አረፉ! – በአሳዛኝ መልኩ!!!

በግራ ፖለቲካ ማህጸን ውስጥ ተጸንሶ፣ የጎሳ ፖለቲካን መልክና ቅርጽ ይዞ የተወለደው ኢህአዴግ ይዞት የመጣውን የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ጠባብና ቡድናዊ አመለካከት ሕገ-መንግስታዊ እውቅና ሰጠው፡፡ በሌሎች ሀገሮች እንደሚታየው የአንድ ሀገር ዜጎች መክረውና ዘክረው የተስማሙበትን ሕገ-መንግስት ማቆም ሲገባቸው፣ የኢትዮጵያ ብሔር/ብሔረሰቦችና ሕዝቦች “ተስማሙበት” የተባለ ህገ-መንግስት የሀገሪቱ ህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ሆኖ ተደነገገ፡፡ የኢትዮጵያም ባለቤቶች ግለሰብ ዜጎቿ መሆናቸው ቀርቶ ብሔር/ብሔረሰቦችና ሕዝቦቿ መሆናቸው ታወጀ፡፡

ኢህአዴግ በፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ ያሰፈራቸውን አጀንዳዎች የሀገሪቱ ህገ-መንግስት አካል እንዲሆኑ ካደረገ በኋላ፣ በተቃውሞው ጎራ የተኮለኮሉትን ሁሉንም ተቃዋሚ ኃይሎች ሰብስቦ አንድ ቅርጫት ውስጥ በማጨቅ “የደርግ ስርዓት ርዝራዦች እና የትምክህተኞች ጎራ”  ብሎ ፈረጃቸው፡፡ “እኔ ጋር የሌላችሁ ሁሉ እዚያኛው ጎራ ውስጥ ናችሁ” በማለትም ደመደመ፡፡ ሕጋዊ፣ መንግስታዊና አስተዳደራዊ ጫናዎችን በመፍጠርም ያራውጣቸው ጀመር፡፡
እንዲህ ዓይነት የፖለቲካ መካረርና ጡዘት በተፈጠረበት ወቅት ነበር በአዲስ ትውልድ የተገነባው፣ አዲስ አስተሳሰብ ያነገበውና አዳዲስ አሰራሮችን የሰነቀው «ኢዴፓ» ብቅ ያለው፡፡ የኢዴፓን መመስረትና የሶስተኛ አማራጭን መከሰት በክፍል ሶስት እናያለን፡፡

10 Comments
Oldest
Newest Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
getachew tsehaye
getachew tsehaye
14 years ago

“……yetesafu asteyaetoch bemetatifu yizet weyim chibt lye yatekoru bayhonum….”

Aya Mergu Damtew, i got a question for you to read your article in the future and to discuss your point as per your wish.

1gna. .. can you please define what “hizb” is? ke tsihufih megbia lye “hizb” malet bileh tinish ginizabe asyezen esti ebakih. mejemeria esti enismama for a common good concept.

hizb malet yetignaw endehone kalabrarahilign ene limut elihalehu huletegna endemalanebih yitawekilign.

eyandandachin be aymiroachin yeminor opinion, view, belief linoren yichilal. ena ke meret eyetenesan ye hizb asteyayet, eminet, amelekaket new eyalu lemawirat weyim lemetsaf mejemeria, we need to be objective to our best.

hizbu endih hone, hizbu ezih geba, hizbu bezaga alefe minamin eyalu metsafina mawirat, tinish tinikake yiteyikal yimesilegnal. eyandandu eyetenesa bemiyamirew menged hizb’n picture kaderege endet megbabat yichalal???? ye wef kwankwa kalhone beker.

tarik
tarik
14 years ago

Good observation. I think this attitude of taking things as black or white and no miidle ground takes many years to change. The ruling party is in a better postion to shape the people by eduating them to be a better society because EPRDF control the media, has got money, etc.. Unfortunately they are the products of ‘that generation’ therefore no hope from that side.

Abba Jihad Muhie
Abba Jihad Muhie
14 years ago

getachew tsehaye፣

ሓሳብህ ጥሩ ነው፡፡ ግን «ሕዝብ» የሚለውን ቃል እንኳን ጸሐፊው የሀገሪቱም ህገ መንግስት ትርጉም አልሰጠውም፡፡ በህገ መንግስቱ ላይ «ብሔር» ማለት፣ «ብሔረሰብ» ማለት፣ «ሕዝቦች» ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትርጉም አልተሰጠውም፡፡ ስለዚህ፣ ወዳጄ ጌታቸው በዚህ አከራካሪ ጉዳይ ላይ «ትርጉም ካልተቀመጠልኝ አልወያይም፣ ጽሑፍህን አላነብም» ማለትህ ጥሩ ስልት አደለም፡፡ ለውይይት እንዲያመች ቢያንስ የራስህን ትርጉም እስቲ አንተ አስቀምጥልን፡፡

brightday
brightday
14 years ago

In this colourfull world of ours its pitty that people see only in black or white. i ve great understanding to your view. the new generation has to fid this way of intrpreting politics an lifa in general.

getachew tsehaye
getachew tsehaye
14 years ago

Let me say some thing. I should confess. To be honest, I, myself, can’t give answer for that definition. But what I should like to insist is one should take maximum care possible to generalize while referring the ethiopian people (like your topic “Tikur ena nech poletikachin” is saying it well ) . To be frank again, You, yourself, wedajie Mergu damtew, are repeating the same tikur ena nech poletika exercise in your article.

Here is my point. We have at least two major scenarios in our country regarding people’s attitude, living situation, belief etc etc. On one hand , I am watching tens of thousands people chanting and dancing that their country is progressing with development. On the other side of the spectrum, I am watching people still suffering their life probably worse than before. I am witnessing both pictures in our country.

Look at such kinds of generalization like, “” …Hizbu tedesete, hizbu biruh tesfa aye, hizbu tesekaye, hizbu tamesse, hizbu gira gebaw….” To my understanding, Mergu, you are on one side of the spectrum trying to convince us Hizbu is not good situation or suffering day in day out.

Tadia ante rasih ke tikur ena nech poletica be min endemitiley, I can’t see that. Are you telling us that there are no people who are happy and positive in ethiopian over all situation these days?

So wedajie Mergu Damtew, with all due respect, what makes your view different from your own heading “tikur ena nech poletica ? Ante erasih generalize eyderk aydel endie?
Stay Well.

በቀለች
በቀለች
14 years ago

ጸሀፊው እንዳሉት የግራ ፖለቲካ በአገራችን ውስጥ የዲሞክራሲ ስርአት እንዳይፈጠርና እንዳይገነባ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጎአል:: ወይ ከኛ ጋር ነህ ወይ ደግሞ ከነሱ ጋር ነህ የሚለውን ተማርን የሚሉ ሰዎች ሳይቀሩ በዛ አስተሳሰብ ውስጥ ተዘፍቀው ማየት ተስፋ ያስቆርጣል:: አንዳንድ ተማርን የሚሉ ሰዎች እንዴት እንዴት እንደሚያስቡ ለማየት ሩቅ መሄድ አያስፈልግም:: የፕሮፈሰር አለማየሁ ገ/ማርያምን ሚዛን ያልጠበቁ ጽሁፎች ማንበብ በቂ ነው::
ከዚሁ የግራ ፖለቲካ ባሻገር ባህላችንም አስተዋጽኦ አድርጎአል ማለት ይቻላል:: በአብዛኛው ቤተሰብ አዋቂ ብቻ ይናገር; ልጅ ዝም ብሎ ማዳመጥ አለበት እየተባለ ያደገ ልጅ ሲያድግ ተመሳሳይ ባህርይ በሌሎች ላይ ቢያሳይ አይደንቅም::

Mergu D.
Mergu D.
14 years ago

getachew tsehaye,
Thank you for your comments and concern to your beloved country. As to my stand, stay tuned!, you will see where I am. ATICHEKUL ESHI?
Bye! for now.

getachew tsehaye
getachew tsehaye
14 years ago

eshi alchekulim, etebikalehu. tenekezchekezchu aydel? benegerachin lye, don’t get me wrong. i’m not totally against your argument. i happen to share most of your points except for the only one i felt dissapointement in your generalization regarding the “hizb’.

stay well my dear.

Abba Jihad Muhie
Abba Jihad Muhie
14 years ago

To me what matters is not to know the stand of the writer, but to know the process of our politics and the way forward, what should we do? I hope the writer will consider these points.

ዳውላ
ዳውላ
13 years ago

ብሔር ማለት ምን ማለት ነው
ብሔረሰብ ማለት ምን ማለት ነው
ብሔር ብሔረሰብ ምን ማለት ነው
ብሔራዊ መለት ምን ማለት ነው
ህዝብ ማለት ምን ማለት ነው