ኢዴፓ መንግስት ነዳጅን እንዲደጉም መግለጫ አወጣ

መንግስት እንዲህ ዓይነት ተራ ትንታኔ እያቀረበ በመዘናጋቱ በአገሪቱ የተከሰተው የኑሮ ውድነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣት ዛሬ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ኢዴፓ በመግለጫው ላይ አስታውቋል። አያይዞም፤ “መንግስት ይህንን በአገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚም ሆነ በህዝቡ የእለት ከእለት ኑሮ ላይ ከፍተኛ አደጋ እያስከተለ የሚገኘውን ችግር ለማቃለል የሚያስችል እርምጃ ይወስዳል ተብሎ በሚጠበቅበት በአሁኑ ወቅት በነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ሊባል የሚችል የዋጋ ጭማሪ” ማድረጉ ተገቢ አደለም ሲል ኢዴፓ የመንግስትን እርምጃ አውግዟል።

በነዳጅ ዋጋ ላይ የሚደረግ ጭማሪ በባህሪው የኑሮ ውድነትን የማባባስ አዝማሚያ እንዳለው በሀገሪቱ ተደጋግሞ መታየቱን ኢዴፓ በሰጠው በዚሁ መግለጫ አስታውሶ፣ ህዝቡ የወቅቱን የኑሮ ውድነት መቋቋም ተስኖት በጣር ላይ በሚገኝበት በዚህ ወቅት “ሕዝባዊ ነኝ” የሚለው መንግስት እንዲህ ዓይነት እርምጃ መውሰዱ ዛሬም የችግሩን አሳሳቢነት እንዳልተገነዘበና ለጉዳዩ ትኩረት እንዳልሰጠው ያሳያል ብሏል ኢዴፓ።

“ስለሆነም” ይላል ኢዴፓ በመግለጫው መቋጫ ላይ፣ “ስለሆነም፣ አንደኛ በነዳጅ ዋጋ ላይ ጊዜአዊ ድጎማ ማድረግ፣ ሁለተኛ የደመወዝና የጡረታ አበል ጭማሬ ማድረግ፣ ሶስተኛ ከኑሮ ውድነት ጋር ተያያዥነት ባላቸው ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ቅነሳ ማድረግ፣ አራተኛ ተደራራቢ የተጨማሪ እሴት ታክስ አሰራራርን ማስቀረት፣ አምስተኛ ጊዜአዊ የመንግስት የካፒታል በጀት ቅነሳ ማድረግ፣ ስድስተኛ የዋጋ ንረት በሚታይባቸው ምርቶች ላይ አቅርቦትን ማሳደግ፣ ሰባተኛ የዋጋ ንረትን በሚያባብሱ ነጋዴዎች ላይ ተገቢውን ህጋዊ ቁጥጥር ማድረግ” የሚሉ የመፍትሄ ሃሳቦችን አቅርቧል።

በመጨረሻም፤ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ህዝብም ጉዳዩን በዝምታ ከማየት ይልቅ በመንግስት ላይ አስፈላጊውን ህጋዊና ሰላማዊ ግፊት እንዲያደርግ ኢዴፓ በሰጠው መግለጫ ጥሪውን አቅርቧል።

0 0 votes
Article Rating
9 Comments
Oldest
Newest Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments
brightday
brightday
13 years ago

thats the mark of a responsible pary. Show the way to the brigher future. Viva EDEPA

ABE
ABE
13 years ago

tHIS WORLD IS CREATED FOR ELITES NOT FOR POOR PEOPLE SO EVERYWHERE THE LIVING STANDARD IS HIGH AND DIFFICULT NOT ONLY IN ETHIOPIA.

dave
dave
13 years ago

For time being subsidizing oil is the best solution to control inflation at large the safety of society.

gashaw
gashaw
13 years ago

It is a timely press release but I think the government will find it painful to do the subsidy. In my openion,not doing it might hamper the government’s five-year ‘Growth and Transformation Plan’ (GTP)

Tazabi
Tazabi
13 years ago

Good work Ethiofacts. I am enjoying your report from Ethiopia.Any way,the struggle is at home and we need to know more about home from someone who lives at home. Period!

Selamawit
Selamawit
13 years ago

As always, EDP is leading the way. This topic is the concern of literally almost all Ethiopians. That is what we expect from a resposnible and matured party. Bravo EDP!!

Nkuto leab
Nkuto leab
13 years ago

I appriciate as usuall EDPs wise move and burning issue.EDP is doing what is possible and good for the nation. Bravo EDP
THE PARTY OF CONCERNED AND CIVILISED PEOPLE!!!!!!!!

Roha
Roha
13 years ago

That is what Ethiopians need. Understand the Reality and propose possible solutions. Wise Ethiopians are understanding your effort.
Not dreaming only power or death.

andinet
andinet
13 years ago

EDP is the party of the people for the people. The soulutions listed sound good but difficult to implement. But it allerts the government to design acceptable soulutions and strategies to control inflation.