Ethiopian Proverbs – ምሳሌዎች
2. ቀና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ
3. አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል
4. አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል
5. ያለ አንድ የላት ጥርስ በዘነዘና ትነቀስ
6. የምታቦካው የላት የምትጋግረው አማራት
7. የጅብ ፍቅር እስኪቸግር
8. አላርፍ ያለች ጣት ስትጠነቁል ትያዛለች
9. በሬ ከአራጁ ይውላል
10. በቅሎ ግዙ ግዙ አንድ አሞሌ ጨው ላያግዙ
11. ዘመድ ከዘመዱ አህያ ከአመዱ
12. ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
13. አይጥ ሞቷን ስትሻ ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ
14. ከድጡ ወደ ማጡ
15. የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል
16. የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ
17. አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል
18. በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት
19. አልሸሹም ዞር አሉ
20. ታጥቦ ጭቃ
21. የቆጡን አወርዳለሁ ብላ የብብቷን ጣለች
22. ለሰው ብሎ ሲያማ ለኔ ብለህ ስማ
23. ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይከፋሽ
24. ባጎረስኩት እጄ ምነው መነከሴ
25. እጸድቅ ብዬ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች
26. ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል
27. ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ፀሎት
28. ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም
29. የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል
30. አያዘልቅ ፀሎት ለቅስፈት
31. ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ
32. ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ
33. ያልጠረጠረ ተመነጠረ
34. አዛኝ ቅቤ አንጓች
35. ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ
36. ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ
37. ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል
38. አህያውን ፈርቶ ዳውላውን
39. ሴት የላከው ሞት አይፈራም
40. ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል
41. ስራ ለሰሪው እሾህ ለአጣሪው
42. አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ
43. ተልባ ቢንጫጫ በአንድ ሙቀጫ
44. አመድ በዱቄት ይስቃል
45. ላለፈው ክረምት ቤት አይሰራለትም
46. የፈሰሰ ውሀ አይታፈስም
47. አትሩጥ አንጋጥ
48. መቀመጥ መቆመጥ
49. ካለ ፈጣሪ አሟጠሽ ጋግሪ
50. የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው
51. ስጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አንድ አለ
52. ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ
53. አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት መጽሀፍ አጥባ ቆየች
54. የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ
55. እሱ የከፈተውን ጉሮሮ ሳይዘጋው አያድርም
56. ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ
57. አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ
58. ንገረው ንገረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው
59. አታግባና የሰው አጥር ዝለል
60. ከስስታም አንድ ይወድቀው አንድ ይተርፈው
61. ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት
62. ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል
63. አተርፍ ባይ አጉዳይ
64. አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል
65. የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ
66. ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል
67. ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሀምሳ ሰው ጌጡ
68. እውነቱን ተናግሮ ካመሹበት ማደር
69. ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
70. ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል
71. ከእጅ አይሻል ዶማ
72. በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ
73. የአህያ ባል ከጅብ አያስጥል
74. ከወፈሩ ሰው አይፈሩ
75. ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት
76. ሲስሟት ቀርቶ ሲስቧት
77. ቀድሞ ማን ቢስምሽ ታሞጠሙጫለሽ
78. እግረ ቀጭን ይሞታል ሲሉ እግረ ወፍራም ይቀድማል
79. ያልታደለ ከንፈር ሳይሳም ያረጃል
80. በቦሃ ላይ ቆረቆር
81. የቸገረው እርጉዝ ያገባል፣ የባሰበት እመጫት
82. የአህያ ስጋ አልጋ ሲሉት መሬት
83. ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም
84. የደላው ሙቅ ያኝካል
85. የፈሪ ዱላው ረጅም ነው
86. የፈሪ በትር ሆድ ይቀትር
87. ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ ንጣት ይገለው ነበር
88. ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ
89. ተንጋለው ቢተፉ ተመልሶ ካፉ
90. ሰዶ ማሳድድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ
91. ዞሮ ዞሮ ወደቤት ኖሮ ኖሮ ወደ መሬት
92. ራሴን ሲበላኝ እግሬን ቢያኩኝ አይገባኝም
93. የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም
94. ከዕባብ እንቁላል እርግብ አይፈለፈልም
95. አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው
96. ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ
97. በአንድ ራስ ሁለት ምላስ
98. ብላ ባለኝ እንዳባቴ በቆመጠኝ
99. የድሀ ቅንጡ እንጀራ ሲሰጡት ይላል ድልህ አምጡ
100. ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል
101. ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል
102. ወረቀትና ሞኝ የያዘውን አይለቅም
103. አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ባሰብሽ
104. ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም
105. ዘመደ ብዙ ጠላው ቀጭን ነው
106. ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል
107. ከድሀ ከመበደር ከባለጸጋ መስረቅ ይቀላል
108. ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል
109. ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አያስታውቅም
110. የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም
111. አስቀድሞ ነበር መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ይሰራል ድስት ድጦ ማልቀስ
112. ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም
113. ጭብጥ ቆሎ ይዘህ ወደ አሻሮ ተጠጋ
114. ውሀ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው
115. የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ
116. ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ
117. ልጅን ሲወዱ እስከነ ንፍጡ ነው
118. መልካም ስም ከመልካም ሽቶ ይበልጣል
119. ሰውና እንጨት ተሰባሪ ነው
120. ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች
121. ሰው ጥራ ቢሉት ራሱ መጣ
122. ምንም ብቀጥን ጠጅ ነኝ
123. በቅሎን አባትሽ ማነው ቢሏት እናቴ ፈረስ ነች አለች
124. ቀጥኜ ቢያየኝ ጅማት ለመነኝ
125. የአዝማሪ ሚስት አልቅሰው ካልነገሯት አይገባትም
126. ምነው እናቴ እንቁላል ስሰርቅ በቀጣችኝ
127. ዶሮ ብታልም ጥሬዋን
128. ዶሮ ጭራ ጭራ መታረጃዋን ታወጣለች
129. አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል
130. የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር
131. ወሬ ቢበዛ በአህያ አይጫንም
132. ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ
133. የማያውቁት አገር አይናፍቅም
134. ዳሩ ሲወረር መሀሉ ዳር ይሆናል
135. መካሪ የሌለው ንጉስ አንድ አመት አይነግስ
136. ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ
137. የአገሩን መሬት በአገሩ በሬ
139. ታሞ የተነሳ እግዜርን ረሳ
140. ለጌታም ጌታ አለው
141. ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል
142. ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ
143. ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ
144. ሰውን ማመን ቀብሮ አለች ቀበሮ
145. ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም
146. ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለእዳ አይቀበለውም
147. ከሞመት መሰንበት
148. የወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል
149. አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ
150. እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አለች አህያ
151. ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም
152. በአንድ ራስ ሁለት ምላስ
153. በሁለት ቢላዋ መብላት
154. የሽሮ ድንፋታ ከእሳት እስኪወጣ
155. በለፈለፉ ባፍ ይጠፉ
156. ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ
157. ሁለት ሰላምታ አንዱ ለነገር ነው
158. የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል
159. የላጭን ልጅ ቅማል በላት
160. በሬ ሆይ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ
161. ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በተኮነንኩኝ
162. ያልሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል
163. ለቀባሪው አረዱት
164. ማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ
165. ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ
166. ጅብ በቀደደው ውሻ ይገባል
167. ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች
168. ዛፍ ያጣ ጉሬዛ
169. ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው
170. አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል
171. ከልጅ አትጫወት ይወጋሃል በእንጨት
172. ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ
173. ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ
174. ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ
175. አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም
176. የዕብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል
177. ለወሬ የለው ፍሬ
178. በሽታውን የደበቀ መድሀኒት አይገኝለትም
179. ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም
180. ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ
181. ትለብሰው የላት የምትከናነበው አማራት
182. የበላችው ያገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታል
183. እንኳን ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ
184. በባዳ ቢያኮርፉ: በጨለማ ቢያፈጡ: ምን ሊያመጡ
ተጨማሪ
የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎች
በዳንኤል አበራ
እዚህ ይጫኑ (PDF 377KB)