የአዲስ አበባ ቆይታዬና ትዝብቴ ክፍል 3

የአዲስ አበባ ቆይታዬና ትዝብቴ (ክፍል ሦስት)

በፍሬው አበበ

ከክፍል 2 የቀጠለ

8. “ወያኔ ይማረኝ”

በአዲስ አበባ ቅይታዬ በጣም የታዘብኩት፣ የአብይ የኦህዴድ አስተዳደር እጅግ በጣም በህዝቡ ተጠልቷል። ከካድሬዎች በስተቀር ስለ አብይ ጥሩ የሚናገር ገለልተኛ ሰው ማግኘት ከባድ ነው። በጣም የገረመኝ ነገር ደግሞ የአብይ ኦህዴድን ከመለስ ሕወሃት ጋር በማወዳደር፣ ካለማመንታት “ዘመነ ወያኔ” ይሻላል የሚሉ ብዙ ሰዎች ማግኘቴ ነው ።

ለምን የአብይ ኦህዴድ የከፋ እንደሆነ ለማስረዳት ለንጽጽር የሚሰጧቸው ምክንያቶች ሚዛን የሚደፉ ሆነው አግኝቻቼዋለሁ። የኑሮ ደረጃ ማሽቆልቆል፣ በኃይማኖቶች ጣልቃ መግባት፣ በጦርነት መላ አገሪቱ መታመስ፣ ከአዲስ አበባ ውጪ በሰላም በመኪና ወጥቶ መግባት አለመቻል፣ እገታ መስፋፋት፣ አይን ያወጣ ተረኝነት፣ የኑሮ ውድነት፣ መፈናቀል፣ ከስራ መባረር፣ ቤት መፍረስ፣ የንብረት ባለኔትነት ዋስትና አለመኖር፣ ….ይዘረዘራሉ።

እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው፣ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግሮች በአብዛኛው የተፈጠሩት በሕወሃት ነው። በእርግጥ የአብይ ኦህዴድ እራሱ የጨመራቸው ችግሮች አሉ። ሕወሃት እንደ ድርጅት መለስ እንደ ግለሰብ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ስልጣን በፍጹም መያዝ አልነበረባቸውም። ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ አብዝተቶ የሚጠላት ግለሰብና (መለስ) ፓርቲ ( ሕወሃት) ላይ ወድቃ ነበር።

በማናቸውም ሀገር በህግ የተከለከለው፣ የብሄር ፓለቲካና የጎሳ ባንቱስታን የአፓርታይድ ክልሎች ተቋም ተበጅቶለት የተተከለው በወያኔ ነው። የሕወሃት ጠባብ ጎጠኛ የአንድ ድርጅት የፓለቲካ ፕሮግራም፣ እንደ ወረደ ወደ የኢትዮጵያ “ህገመንግስት” ተቀይሯል። የሁሉም አውዳሚ የአፓርታይድ የባንቱስታን ልዩ ኃይሎች ከህግ ውጪ በሕወሃት ተቋቁመዋል።

ኢትዮጵያ የባህር በር ብቻ ሳይሆን መላ ኤርትራን ያጣችው “የሽግግር መንግስት” በነበረ ማንዴት ባልነበረው በወያኔ ታላቅ ሴራ ነው። ለ27 ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ ከፍተኛ የሚሊቴሪና የደህንነት ቦታዎች ሙሉ ለሙሉ የወደቁት 5% በታች በነበረ አናሳ ህብረተሰብ በወጡ የአድዋ ገዢ መደብ ነበር።

Of two evils, choose neither እንደሚባለው፣ ከወያኔና ከኦህዴድ መካከል ማማረጥ መሞከር፣ ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ ነው። ባጭሩ የአብይ ኦህዴድን መጥላት፣ ወያኔን እንድንናፍቅ ሊያደርገን በፍጹም አይገባም። ምክንያቱም ለአብይ ኦህዴድ ለሚሰራው መጥፎ ስራዎች ሁሉ መሰረቱ ወያኔ ተቋሞች አበጅቶ የተከለው የጎሳ ስርዓት ነው።

9. የፓሊስ ብዛት/ police state

አዲስ አበባ ከመቼውም በተለየ ሁኔታ በፓሊስ ተጨናንቃለች። መሃል ከተማ ውስጥ በየ50 ሜትር ርቀት ጥንድ ጥንድ የለበሱ የአዲስ አበባ ፓሊሶች ይታያሉ። ከአዲስ አበባ ፓሊሶች በተጨማሪ እንዲሁ ዩኒፎርም የለበሱ ጠባቂዎች ይታያሉ። አዳነች አበቤ አሰልጥና ያሰማራቻቸው ጠባቂዎች ናቸው።

የኦሮሞ ፓሊስ ደግሞ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች በካምፕ በካምብ ከትሟል። ሳር ቤት፣ 6 ኪሎ መነን ት/ቤት ፊት ለፊት፣ በቅሎ ቤት፣….። አዲስ አበባ ውስጥ የኦሮሞ ባንቱስታን ፓሊስ ምን ያደርጋል? ጭራሽ በቅሎ ቤት ሌት ተቀን የሚጠበቅ፣ በአካባቢው መኪና ማቆም የማይቻልበት፣ እግረኛ የማያልፍበት፣ የኦሮሞ ባንቱስታን ፓሊስ ዋና መምርያ ህንጻ ተገንብቶ አልቋል።

አብይ ላይ መፈንቅለ መንግስት ቢካሄድ፣ “መንግስቴ ተነካ” ብለው እንዲያከሽፉለት ታስቦ ይሆን? ከአዲስ አበባ ህዝብ ብዛት አንጻር ባህር ውስጥ እምቡር እምቡር የሚሉ አሳዎች መሆናቸውን ገና ኦህዴድ አልገባውም ማለት ነው? የአዲስ አበባ፣ የፌዴራል ፓሊስንና የአዳነች አበቤ ታጣቂዎች ታማኝነት በቂ አይደለም ማለት ነው?

ድንገተኛ የመኪና ፍተሻ በየቦታው አለ። አንድ አንድ ሰፈር ለምሳሌ አቧሬ ምናልባትም በቤተ መንግስት ዙሪያ ስለሚገኝ ቤት ለቤት ሳይቀር ፍተሻ በተደጋጋሚ ይደረጋል።

ይሄ ሁሉ የፓሊስ ብዛት ህዝቡን ከመፍራት የመነጨ እንደሆነ ይገባኛል። የአብይ የኦህዴድ ገዢ መደብ የአዲስ አበባ ህዝብን እንደ ጠላት እንደሚቆጥሩት ግልጽ ነው።

እስከ መቼ ነው እንዲህ የአዲስ አበባን ህዝብ ኦህዴድ ፈርቶ የሚዘለቀው? ለዚሁ ሁሉ ታጣቂ ያውም እየተንኮታከተ እየሄደ ባለ ኢኮኖሚ ደሞዝ እየከፈሉ መቀጠል ይቻላል? አንድ አንድ የፓለቲካ ተንታኞች እንደደሚሉት የአብይን መንግስት ከታጣቂዎች በፊት የኢኮኖሚው ችግር አሽቀንጥሮ ሊጥለው ይችላል። የአህያ ባል ከጅብ አያስጥል እንደሚባለው፣ ህዝብ የቆረጠ ቀን ፓሊስ ሳይቀር ጠመንጃውን እንደሚያዞር ከቅርቡ የራሳችንም ወይም የተለያዩ ሀገሮች ታሪክ መማር ተገቢ ነበር።

10. የተወሰኑ የተጠኑ የአዲስ አበባ ተቋሞች ውስጥ የኦህዴድ ተረኝነት

አዲስ አበቤዎች መገፋታቸውን፣ መገለላቸውን፣ እንደ 3ኛ ዜጋ መቆጠራቸውን፣ የኦህዴድን አይን ያወጣ ተረኝነት መገለጫ አድርገው ከሚያቀርቧቸው መስሪያ ቤቶች መካከል በኦህዴዱ አቤ ሳኜ የሚመራው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በኦህዴዷ አዳነች አቤቤ የሚመሩት የአዲስ አበባ ትራፊክ ፓሊስ፣ የአዲስ አበባ ፓሊስ፣ የወረዳ አስተዳደር ቢሮዎች በስፋት ይጠቀሳሉ።

ወረዳ ውስጥ ለአዲስ አበባ ባዕድ የሆኑ፣ የአዲስ አበባን ህዝብ ስነልቦና አሁን ድረስ መረዳት ያልቻሉ፣ ቁቤ እንጂ አማርኛ የማያነቡ የሰነድ ማረጋገጫ ኃላፊዎች ሳይቀር እንዳሉ ሰምቻለሁ። ጭራሽ በአማርኛ የተጻፈው ሰነድ ምንድነው የሚለው ብሎ ተገልጋዩን መልሶ የጠየቀ የወረዳ የኦህዴድ ባለጊዜ ኃላፊ እንዳጋጠመው አንድ ወዳጄ ነግሮኛል።

ብሄራዊ ቤተመንግስትን፣ የአጼ ሚኒሊክ ቤተመንግስትን፣ አድዋ ሙዝየምን ጎብኝቻለሁ። ትኬት ቆራጮቹ፣ አስጎብኚዎቹ፣ የጥበቃ ሰራተኞቹ፣ የጽዳት ሰራተኞቹ፣…… በአብዛኛው የኦሮምኛ ተናጋሪዎች መሆናቸውን አስተውያለሁ።

ብዙ ሻጥር ያለበትን በሕወኃት በመጨረሻ ላይ የተደረገውን የህዝብ ቆጠራ ብንወስድ እንኳን፣ ወደ 73% የአዲስ አበባ ህዝብ አማራና ጉራጌ ነው። የኦህዴድ በአዲስ አበባ ባለጊዜነት ይሄን መሬት ላይ ያለውን ሃቅ ስለሚጋጭ ነው በአዲስ አበቤዎች የተናቀው የተጠላው።

 

Related:
የአዲስ አበባ ቆይታዬና ትዝብቴ (ክፍል-1)

የአዲስ አበባ ቆይታዬና ትዝብቴ (ክፍል-2)

guest

0 Comments
Oldest
Newest Most Voted
Inline Feedbacks
View all comments

0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x