የአማርኛ ምሣሌያዊ አነጋገሮች
151 | ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም |
152 | በአንድ ራስ ሁለት ምላስ |
153 | በሁለት ቢላዋ መብላት |
154 | የሽሮ ድንፋታ ከእሳት እስኪወጣ |
155 | በለፈለፉ ባፍ ይጠፉ |
156 | ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ |
157 | ሁለት ሰላምታ አንዱ ለነገር ነው |
158 | የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል |
159 | የላጭን ልጅ ቅማል በላት |
160 | በሬ ሆይ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ |
161 | ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በተኮነንኩኝ |
162 | ያልሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል |
163 | ለቀባሪው አረዱት |
164 | ማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ |
165 | ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ |
166 | ጅብ በቀደደው ውሻ ይገባል |
167 | ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች |
168 | ዛፍ ያጣ ጉሬዛ |
169 | ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው |
170 | አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል |
171 | ከልጅ አትጫወት ይወጋሃል በእንጨት |
172 | ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ |
173 | ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ |
174 | ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ |
175 | አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም |
176 | የዕብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል |
177 | ለወሬ የለው ፍሬ |
178 | በሽታውን የደበቀ መድሀኒት አይገኝለትም |
179 | ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም |
180 | ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ |
181 | ትለብሰው የላት የምትከናነበው አማራት |
182 | የበላችው ያገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታል |
183 | እንኳን ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ |
184 | በባዳ ቢያኮርፉ: በጨለማ ቢያፈጡ: ምን ሊያመጡ |
ለተጨማሪ ምሳሌዎች እታች ይጫኑ