የአዲስ አበባ ቆይታዬና ትዝብቴ ክፍል 3

የአዲስ አበባ ቆይታዬና ትዝብቴ (ክፍል ሦስት)

በፍሬው አበበ ከክፍል 2 የቀጠለ 8. “ወያኔ ይማረኝ” በአዲስ አበባ ቅይታዬ በጣም የታዘብኩት፣ የአብይ የኦህዴድ አስተዳደር እጅግ በጣም በህዝቡ ተጠልቷል። ከካድሬዎች በስተቀር ስለ አብይ ጥሩ የሚናገር ገለልተኛ ሰው ማግኘት ከባድ ነው። በጣም የገረመኝ ነገር ደግሞ የአብይ ኦህዴድን ከመለስ ሕወሃት ጋር በማወዳደር፣ ካለማመንታት “ዘመነ ወያኔ” ይሻላል የሚሉ ብዙ ሰዎች ማግኘቴ ነው ። ለምን የአብይ ኦህዴድ የከፋ እንደሆነ ለማስረዳት ለንጽጽር የሚሰጧቸው ምክንያቶች ሚዛን የሚደፉ ሆነው አግኝቻቼዋለሁ። የኑሮ ደረጃ ማሽቆልቆል፣ በኃይማኖቶች ጣልቃ መግባት፣ […]