ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሚለው የመለስ ፈጠራ ምንጩ ማነው?

በያሬድ ኃይለመስቀል ብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች የሚለው ቃል ትልቁ የማይደፈር እና የሚፈራ ጣኦት ሆኖ ለ34 ዓመት ገዝቷል። ይሄንን ቃል መተቸት የሚያሰገድል የሚያስገርፍ የሚያሳስር ነበር። እሱ የብሔር ብሔረሰቦች ጠላት ነው የሚለውን ክስ ሁሉን ብርክ የሚያስይዝ ቃል ነበር። በመንግስቱ ግዜ ጸረ-አብዮተኛ፣ አናርኪስት፣ ፊውዳል ከባሚለው ክስ በላይ የሚያስፈራ ነበር። እነኚህ ጸረ ስርአትና መንግስት ስያሜዎች ናቸው። ጸረ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ማለት ግን የህዝብ ንቀት ተብሎ የሚያስከስስና ምህረት የሌለው ወንጀል ነበር። ታድያ እነዚህን ቃሎች መለስ ከየት ተዋሳቸው። […]