“አወዛጋቢ ቦታዎች”፣ መጪው “ምርጫና የፍርድ ቤት” ጉዳይ

በአበራ ገ/ማርያም ምንም እንኳን የኦህዴድና የሕወሃት የፕሪቶሪያ ስምምነት “አወዛጋቢ ቦታዎች” ባሉበት ማለትም በአማራ ክልል ባንቱስታን እጅ ቆይተው በህገ መንግስት/ ህገ ሕወሃት መሰረት የዘለቄታ መፍትሄ ይሰጣቸዋል ቢልም፣ ሲጀምር “አወዛጋቢ ቦታ” የሚባል ነገር የለም። የፕሪቶሪያ ስምምነት “አወዛጋቢ ቦታዎች” የሚላቸው ሕወሃት ከጻፈው የሽግግር መንግስት ቻርተርና ህዝቡ ላይ በኃይል ከጫነው ህገ መንግስት በፊት፤ ወልቃይትን ከጎንደር ራያን ከወሎ ክ/ሀገር በጠራራ ፀሃይ ወደ ትግራይ ክ/ሀገር በኢምፔሪያል ሕወሃት የተጠቃለሉ ናቸው። እባብ የሆዱን አይቶ እግር ነሳው ሆኖ እንጂ፣ […]